በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለራሱ የሚሆን ቅጂ ማስቀረት አልቻለም

ለራሱ የሚሆን ቅጂ ማስቀረት አልቻለም

ለራሱ የሚሆን ቅጂ ማስቀረት አልቻለም

አንድ ነጋዴ በስሎቬኒያ ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲህ ሲል ጻፈ:-

“ያለማቋረጥ ንቁ! እና መጠበቂያ ግንብ መጽሔቶች ስለምትልኩልኝ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። በጉዞ ላይ እና ለንግድ ጉዳይ የሚደረጉ ስብሰባዎች እስኪጀምሩ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ስለማነብባቸው ወደ አንድ ቦታ ስጓዝ ይዣቸው እሄዳለሁ።

“እንዲሁም መጽሔቶቻችሁ ላይ ተጠቅሰው የነበሩትን ስለ አንተ የሚያስብ ፈጣሪ ይኖር ይሆን? (እንግሊዝኛ)፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? እና ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባሉትን ጽሑፎች እንድትልኩልኝ እፈልጋለሁ።

“የእያንዳንዱን ጽሑፍ ሁለት ቅጂዎች እንድትልኩልኝ እፈልጋለሁ። ይህም በጉዞ ላይ እያለሁ የእናንተን ጽሑፍ በማነብበት ጊዜ ሁሉ የማነበውን ነገር ለማወቅ ከፍተኛ ጉጉት ያለው አንድ ሰው ስለማይጠፋ ነው። ጽሑፉን ለግሌ ቤተ መጻሕፍት የማስቀመጥ ፍላጎት ቢኖረኝም እንኳ ለሰውዬው የራሴን ቅጂ እሰጠዋለሁ።”

የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? የተባለውን ግሩም የሆነ ባለ 32 ገጽ ብሮሹር በማንበብ እርስዎም ከፍተኛ ጥቅም እንደሚያገኙ እርግጠኞች ነን። ይህ ጽሑፍ ፈጣሪያችን በቅርቡ ፍጻሜውን የሚያገኝ ታላቅ ዓላማ እንዳለው ያሳያል። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።

የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? የተባለውን ብሮሹር ማግኘት እፈልጋለሁ። በየትኛው ቋንቋ እንደሚፈልጉ ይጥቀሱ

□ ያለ ክፍያ የሚደረገውን የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በተመለከተ እንድታነጋግሩኝ እፈልጋለሁ።