በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“መታመን ያለብኝ በአምላክ ነው”

“መታመን ያለብኝ በአምላክ ነው”

“መታመን ያለብኝ በአምላክ ነው”

የሚከተለው ደብዳቤ በኢድሞንቶን፣ አልቤርታ፣ ካናዳ በሚገኝ የይሖዋ ምሥክሮች መንግሥት አዳራሽ ውስጥ የተገኘ ነው።

“ውድ መልእክተኛ:-

“ይህን ደብዳቤ የምጽፈው ምናልባት ሳያውቀው በሕይወቴ ውስጥ ትልቅ ነገር ያከናወነውን ሰው ለማመስገን ነው።

“ከጥቂት ሳምንታት በፊት በእኔና በባለቤቴ መካከል ከፍተኛ ጭቅጭቅ ተፈጥሮ ነበር። ‘ጉዳዩ ቀላል ስላልሆነ የምችለው አይመስለኝም’ ብዬ ተናግሬ ከአፌ ሳልጨርስ ወዲያው የበሩ ደወል አቃጨለ። በር ላይ የቆመው አንድ የይሖዋ ምሥክር ነበር። መደበቅ የምችልበት ጊዜ አልፏል።

“በሩን የከፈትኩት ሐሳቤ በጣም ተከፋፍሎ እያለ ስለነበር ምን እንዳለ አልሰማሁትም ነበር። ‘ልጆች’ እና ‘ቤተሰብ’ የሚሉት ቃላት ግን ትዝ ይሉኛል። ሰውየው ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለ መጽሐፍ ከቦርሳው አወጣ። ርዕሱን ስመለከት እዚያው ማልቀስ ጀመርኩ፤ እንባዬን መግታት አልቻልኩም። ቀና ብሎ አየኝና የረበሸኝ ስለመሰለው ይቅርታ ጠይቆ መጽሐፉን ሰጥቶኝ ሄደ።

“ያከናወነው ትልቅ ነገር ምንድን ነው? የምይዘው የምጨብጠው ሲጠፋኝ አምላክ መፍትሔ ስለሚሰጥ መጨነቅ እንደሌለብኝ እንዳስታውስ ማድረጉ ነው። መታመን ያለብኝ በአምላክ ነው። አምላክ መልእክተኛ እንኳ ሳይቀር ይልካል። አመሰግናለሁ።”

ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለው መጽሐፍ እያንዳንዱን የቤተሰብ አባል ሊጠቅም ይችላል። ትምህርት ሰጪ ከሆኑት ምዕራፎቹ መካከል “ቤተሰባችሁን ጎጂ ከሆኑ ተጽዕኖዎች ጠብቁ፣” “በቤተሰባችሁ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን አድርጉ” እና “ቤተሰብን የሚያናጉ ችግሮችን መቋቋም ትችላላችሁ” የሚሉት ይገኙበታል።

የግል ቅጂ ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይላኩ። ችግሮችን ለመፍታት የሚጠቅሙና ፈጣሪ አስቦት እንደነበረው የቤተሰብ ሕይወት አስደሳች እንዲሆን የሚያደርጉ ግልጽ ሐሳቦች ማግኘት ይችላሉ።

ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ ያለ ክፍያ የሚደረገውን የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በተመለከተ እንድታነጋግሩኝ እፈልጋለሁ።