በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የጦርነት ሰለባዎች የተለያዩ ገጽታዎች

የጦርነት ሰለባዎች የተለያዩ ገጽታዎች

የጦርነት ሰለባዎች የተለያዩ ገጽታዎች

“የዛሬዎቹ ጦርነቶች ከጥንቶቹ የተለዩ ናቸው።” ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው የጦርነት ሰለባዎች “ወታደሮች ሳይሆኑ ተራ ዜጎች ናቸው” ሲል በተመድ ራዲዮ የሚሰራጨው “ፐርስፔክቲቭ” የተባለው ፕሮግራም ዘግቧል። ለምሳሌ ያህል በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ወቅት የጦርነቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል ሲቪሎቹ 5 በመቶ ብቻ ነበሩ። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ግን የሲቪል ሰለባዎች ቁጥር ወደ 48 በመቶ አሻቀበ። በዛሬው ጊዜ ደግሞ “በግጭቶች ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች በሙሉ ማለት ይቻላል፣ (90 በመቶ የሚሆኑት) ሲቪሎች ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል አብዛኞቹ ሴቶች፣ ልጆችና አረጋውያን ናቸው።”

በልጆችና በትጥቅ ትግል ጉዳይ የተመድ ዋና ጸሐፊ ልዩ መልእክተኛ የሆኑት ኦላራ ኦቱኑ እንዳሉት ከሆነ “ከ1987 ወዲህ በትጥቅ ትግል ሳቢያ ወደ ሁለት ሚልዮን የሚገመቱ ሕፃናት አልቀዋል።” ይህ ማለት ባለፉት 12 ዓመታት በየቀኑ ከ450 የሚበልጡ ሕፃናት የጦርነት ሰለባ ይሆኑ ነበር ማለት ነው! ከዚህም በተጨማሪ በዚያው ጊዜ ውስጥ ከስድስት ሚልዮን የሚልቁ ሕፃናት ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል አለዚያም የዕድሜ ልክ የአካል ጉዳተኞች ሆነዋል።

ተመድ እያደገ የመጣውን የጦርነት ሰለባ የሆኑ ሕፃናት ቁጥር መዋጋት የሚችልበት አንዱ መንገድ አሉ ሚስተር ኦቱኑ፣ የሰላም ቀጣናዎችን በማቋቋም ነው። “ልጆች በብዛት የሚገኙባቸው እንደ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎችና መጫወቻ ሥፍራዎች ያሉ ቦታዎች ከጦርነት ነፃ የሆኑ ቀጣናዎች ተደርገው መታየት አለባቸው።” ይሁን እንጂ ይላል የተመድ ራዲዮ፣ ተራ ዜጎች የጦርነት ሰለባ እንዳይሆኑ ተመድ ለመከላከል ይችል ዘንድ “ግጭቶቹን ራሳቸውን ማስወገዱ” ከሁሉ የተሻለ ውጤታማ መንገድ ነው። በእርግጥም የጦርነት ሰለባዎች እንዳይኖሩ ለማድረግ ጦርነትን ራሱን ማስወገድ ያስፈልጋል። ይህ ሊሆን የሚችል ነገር ነውን?

የሰው ልጅ ብዙ ዘመናት ያስቆጠረ የጦርነት ታሪክ ያለው በመሆኑ አብዛኛው የምድር ነዋሪ ሰዎች ምድር አቀፍ ሰላም ሊያመጡ አይችሉም የሚል እምነት ያለው መሆኑ ተገቢ ነው። ይሁን እንጂ የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ አምላክ ይህን እንደሚፈጽም በመግለጽ ተስፋ ይሰጣል:- “እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነትን ይሽራል።” (መዝሙር 46:​9) ይህ የሚሆነው መቼ ነው? አምላክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰላም እንደሚያሰፍን የሰጠው ተስፋ እንደሚፈጸም እርግጠኛ መሆን የምትችለውስ ለምንድን ነው? ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ እባክህ ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ የሆነውን በመጠቀም ለዚህ መጽሔት አዘ​ጋጂዎች ጻፍ። አለዚያም ደግሞ በአካባቢህ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮችን አነጋግር። ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ያለ ክፍያ ቀጥተኛ መልሶች ማግኘት ትችላለህ።

[በገጽ 29 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

UN PHOTO 156450/J. Isaac