በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሴቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል

ሴቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል

ሴቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል

ክርስቲያን ሴቶች በዚምባብዌ የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ግንባታ ወቅት ያበረከቱት ከፍተኛ ድርሻ በታኅሣሥ 12, 1998 ሕንጻውን ለአምላክ ለመወሰን በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ጎላ ተደርጎ ተገልጾ ነበር። አራት ዓመት በፈጀው የግንባታ ሥራ ከዚምባብዌ የመጡትን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ጨምሮ ከብዙ አገሮች የተውጣጡ ፈቃደኛ ሠራተኞች በሥዕሉ ላይ የምታያቸውን ማራኪ ሕንጻዎች ለመገንባት ጊዜአቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ችሎታቸውንና ንብረታቸውን ሰጥተዋል።

ከበስተኋላ የሚታዩት እኩል መጠን ያላቸው ስድስት ሕንጻዎች ለመኖሪያነት የተገነቡ ናቸው። ከመኖሪያ ሕንጻዎቹ አጠገብ ባለው ትልቅ ሕንጻ ውስጥ መመገቢያ ቤቱ፣ ወጥ ቤቱ እንዲሁም የልብስ ንጽህና መስጫው ይገኛል። የመኖሪያ ሕንጻዎቹ 61 መኝታ ቤቶች ሲኖሩአቸው የመመገቢያው አዳራሽ ደግሞ ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎች ያስተናግዳል። ከዋናው መግቢያ በስተግራ በኩል በሚገኘው ሕንጻ ላይ ያሉት ቢሮዎች ናቸው። መሐል ላይ ያለው የእንግዳ መቀበያ ክፍል ሲሆን በቀኝ በኩል ደግሞ ሕንጻዎቹን ለአምላክ አገልግሎት የመወሰኑ ሥነ ሥርዓት የተካሄደበት መጋዘን ይገኛል።

በደቡባዊ አፍሪካ በምትገኘው ዚምባብዌ የተገነባው ይህ ግሩም የቅርንጫፍ ቢሮ ሕንፃ የይሖዋ ምሥክሮች በህዳር 1985 ዓለም አቀፍ የግንባታ ኘሮግራም ከጀመሩ ወዲህ ተሰርተው ከተጠናቀቁት ብዙ የግንባታ ኘሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው። የነሐሴ 22, 1991 ንቁ! መጽሔት (እንግሊዝኛ) “በዓለም አቀፍ የግንባታ ሥራ ረገድ የተከፈተ አዲስ ምዕራፍ” በሚል ርዕስ ስለዚህ ኘሮግራም አብራርቶ ነበር።

በግንባታው ኘሮግራም ላይ ሴቶች የነበራቸውን ድርሻ በተመለከተ ንቁ! መጽሔቱ እንዲህ ሲል ዘግቧል:- “ብዙ ሴቶች የአርማታ ብረት በማሰር፣ የወለል ሸክላ በማንጠፍ፣ በሸክላዎቹ መካከል ያለውን ክፍተት በመሙላት፣ እንዲሁም በማለስለስና ቀለም በመቀባት ለመሳተፍ የሚያስችል ሥልጠና አግኝተዋል። ሌሎች ደግሞ በጣም አስፈላጊ የሆኑ የቤት ውስጥ ሥራዎችን ያከናውናሉ። በዚህ መንገድ ሁሉም በዓለም ዙሪያ በሚደረጉት የግንባታ ሥራዎች ላይ አይነተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።”

በቅርቡ በዚምባብዌ ሕንጻዎቹን ለአምላክ አገልግሎት ለመወሰን በተካሄደው ኘሮግራም ላይ በግንባታው ሥራ የበላይ ተመልካችነት ያገለገሉት ወንድም ጆርጅ ኢቫንስና ወንድም ጀምስ ፖልሰን ቅርንጫፍ ቢሮውን በመገንባቱ በኩል ሴቶች የነበራቸውን ድርሻ የጥንት እስራኤላውያን ሴቶች የመገናኛውን ድንኳን ለመሥራት ካበረከቱት አስተዋጽኦ ጋር በማነጻጸር ተናግረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እስራኤላውያን “ከእነርሱም ሰው ሁሉ ልቡ እንዳነሳሳው አመጡ” ካለ በኋላ “ወንዶችና ሴቶችም . . . አመጡ።” በማለት ይገልጻል።​—⁠ዘጸአት 35:​21, 22፣ በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።

ወንድም ኢቫንስ እና ወንድም ፓልሰን ከላይ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ በመጠቀም የሴቶቹ ተሳትፎ ምን እንደሚመስል በንግግራቸው አጉልተውት ነበር። ‘በልባቸው ጥበበኞች የሆኑ ሴቶችም በእጃቸው ፈተሉ ልባቸውም በጥበብ ያነሳሳቸው ሴቶች ሁሉ ፈተሉ’ የሚለውን ሐሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጠቅሰው ነበር። ሥራውን ለመሥራት ራሳቸውን በፈቃደኝነት ካቀረቡት ብዙ ሰዎች መካከል ሴቶችም ነበሩበት። “ከእስራኤልም ልጆችም ያመጡ ዘንድ ልባቸው ያስነሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ሙሴ ይሠራ ዘንድ እግዚአብሔር ላዘዘው ሥራ ሁሉ ለእግዚአብሔር ስጦታ በፈቃዳቸው አመጡ።”​—⁠ ዘጸአት 35:​25, 26, 29፣ በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።

የዚምባብዌን የቅርንጫፍ ቢሮ ፕሮጀክት በተመለከተ የግንባታው ሥራ የበላይ ተመልካቾች ‘ሴቶቹ ወንዶች የሚሠሩትን ሥራ ሁሉ ሠርተዋል’ በማለት ተናግረዋል። ይህም የአርማታ ብረት ማሰርንና ትላልቅ የግንባታ መሣሪያዎችን ማንቀሳቀስን ይጨምራል። ወንድም ፖልሰን ሴቶቹ ሲሚንቶ ለማመላለስና ለማደባለቅ የሚጠቀሙባቸውን የጭነት መኪናዎች እንዲሁም ሌሎች ትላልቅ የግንባታ መሣሪያዎቻቸውን ንጹህ አድርገው እንደሚተዉና ወንዶቹ ግን በጥቅሉ ሲታይ እንዲህ ዓይነት ዝንባሌ እንደሌላቸው ማስተዋሉን ገልጿል።

በእርግጥም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያን ሴቶች በዓለም አቀፉ የቅርንጫፍ ቢሮዎችና የይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሾች ግንባታ ሥራ ከወንዶች ጎን ተሰልፈው ለሚያከናውኑት ተግባር አመስጋኞች ነን!

[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የዚምባብዌ ቅርንጫፍ ቢሮ