በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ደስተኛ የቤተሰብ ሕይወት መምራት የሚቻልበት መንገድ

ደስተኛ የቤተሰብ ሕይወት መምራት የሚቻልበት መንገድ

ደስተኛ የቤተሰብ ሕይወት መምራት የሚቻልበት መንገድ

በደቡብ አሜሪካ አርጀንቲና ውስጥ የምትኖረው ግራሲየላ “ላለፉት 40 ዓመታት መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔት ሳነብ ቆይቻለሁ” ስትል ጽፋለች። “ዛሬ ከብዙ ዓመታት በኋላ እነዚህ መጽሔቶች በእርግጥ ፍላጎቴን አሟልተውልኛል ለማለት እችላለሁ። ልጅ ሳለሁ፣ በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ በነበርኩበት ወቅት፣ ከተቃራኒ ጾታ ጋር በመጠናናት ላይ በነበርኩበት ጊዜና በትዳር ሕይወቴ ውስጥ እንዲሁም ስድስት ልጆቼን በማሳድግበት ጊዜ ረድተውኛል።

“መጽሔቶቹ አሁንም አብረውን ያሉትን አራት ልጆቻችንን በማሳደግ ረገድ እኔና ባለቤቴን ጠቅመውናል። ልጆቼንና የትምህርት ቤት አስተማሪዎቻቸውን ለማነጋገር በመጽሔቶቹ በጥሩ ሁኔታ እጠቀምባቸዋለሁ። የጤና ችግሮችን በተመለከተ ከዶክተሮች ጋር ስነጋገር በቀጥታ ከንቁ! መጽሔት አነብላቸዋለሁ። “የመማር ችግር ላለባቸው ልጆች የሚሆን እርዳታ” (የካቲት 22, 1997) (እንግሊዝኛ) በሚል የሽፋን ርዕስ ለወጡት ተከታታይ ርዕሶች አመስጋኞች ነኝ። አንደኛዋ ሴት ልጃችን የመማር ችግር እንዳለባት እንድናስተውል አስችሎናል።”

የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የሚያዘጋጃቸው ጽሑፎች ቤተሰቦች የሚያጋጥሟቸውን በርካታ ችግሮች እንዲወጡና አስደሳች የቤተሰብ ሕይወት እንዲመሩ ሊረዷቸው ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለው ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ እያንዳንዱን የቤተሰብ አባል ማለትም ባሎችን፣ ሚስቶችን፣ ወላጆችን፣ ልጆችን፣ አያቶችን ሊጠቅም ይችላል። ትምህርት ሰጪ ከሆኑት ምዕራፎቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:- “ልጆቻችሁን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ አሠልጥኗቸው፣” “በጉርምስና ዕድሜ የሚገኙ ልጆቻችሁን በጥሩ ሁኔታ እንዲያድጉ እርዷቸው፣” “ቤተሰባችሁን ጎጂ ከሆኑ ተጽዕኖዎች ጠብቁ” እና “ቤተሰብን የሚያናጉ ችግሮችን መቋቋም ትችላላችሁ።”

የግል ቅጂ ማግኘት ይችሉ ዘንድ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ። ችግሮችን ለመፍታት ሊረዱ የሚችሉና ፈጣሪያችን አቅዶት እንደነበረው የቤተሰብ ሕይወት አስደሳች እንዲሆን ሊያደርጉ የሚችሉ አንዳንድ ሐሳቦች ያገኛሉ።

□ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ ያለ ክፍያ የሚደረገውን የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በተመለከተ እንድታነጋግሩኝ እፈልጋለሁ።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ግራሲየላ እና ቤተሰቦቿ