ጠፍቶ የነበረውን ማግኘት
ጠፍቶ የነበረውን ማግኘት
ባለፈው ዓመት በዩ ኤስ ኤ ሜሪላንድ ውስጥ አንድ ሰው የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ ! መጽሔቶችን እንዲወስድ ግብዣ ሲቀርብለት መጽሔቶቹን መውሰድ እንደማይፈልግ በአክብሮት ይገልጻል። ይሁን እንጂ ትንሿ ሴት ልጁ መጽሔቶቹን መውሰድ ትችል እንደሆነ ስትጠይቅ አባትየው መውሰድ እንደምትችል ይነግራታል። አባትና ልጅ መኪናቸውን በማጽዳት ቆሻሻውን በአቅራቢያ በሚገኘው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ውስጥ እየጨመሩ ነበር። መጽሔቶቹን ያበረከተላቸው የይሖዋ ምሥክር መጽሔቶቹን ይጥሏቸው ይሆናል የሚል ስጋት ስላደረበት ጥቂት ቆይቶ ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያው ገንዳ በመሄድ ለማረጋገጥ ይወስናል።
ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያው ሄዶ ሲመለከት መጽሔቶቹ አልነበሩም። ሆኖም በቆሻሻ ማጠራቀሚያው ውስጥ የእጅ ቦርሳና የገንዘብ ቦርሳ ተጥሎ ያገኛል። ወዲያውኑ በቦርሳው ውስጥ በነበረው አድራሻ አማካኝነት ሴትየዋን ለማነጋገር ጥረት ተደረገ። ሁለቱ ምሥክሮች ወደ መኖሪያዋ ሲሄዱ በመካከለኛ ዕድሜ ላይ የምትገኝ ሴት አንድን ፈረስ ወደ ጋጥ ስትወስድ ተመለከቱ። ቦርሳዎቿን ሲሰጧት ሴትየዋ “እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ የሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ፣ ፓስፖርቴ፣ የቼክ ደብተሬ፣ የክሬዲት ካርዶቼና የፈረሴ ሰነድ በሙሉ አለ” ስትል በደስታ ስሜት ተውጣ ተናገረች። ቦርሳዎቹን ባለፈው ሌሊት እንደተሰረቀች ገለጸች። የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳው ውስጥ የነበረው ቆሻሻ የሚራገፍበት ጊዜ ደርሶ ስለነበር ምሥክሩ ቀደም ብሎ መሄዱ ጠቅሟታል።
የእጅና የገንዘብ ቦርሳዎቿን የመለሱላት ባልና ሚስት ሴትየዋ ልትሰጣቸው የፈለገችውን ወሮታ ከመቀበል ይልቅ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተሰኘውን ብሮሹር ሰጧት። ሴትየዋ አድናቆቷን ለመግለጽ ስትል ይህን ብሮሹር የመሳሰሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ጽሑፎች በዓለም ዙሪያ ለማሰራጨት ለሚደረገው ጥረት የሚውል ገንዘብ በቼክ ሰጠች። በተጨማሪም ከዚያ ጊዜ አንስቶ መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናት ልባዊ ፍላጎት ሊያድርባት ችሏል።
አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተሰኘውን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ያለ ክፍያ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተሰኘውን ብሮሹር ማግኘት እፈልጋለሁ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።