በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ፍቅር እውር በሚሆንበት ጊዜ

ፍቅር እውር በሚሆንበት ጊዜ

ፍቅር እውር በሚሆንበት ጊዜ

ስፔይን የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንዳጠናቀረው

ዓይንህ ሩቅ ማየት የማይችል ቢሆንና በማታ ካልሆነ በስተቀር የምትስማማህን ፍቅረኛ ማግኘት የማትችል ብትሆን የትዳር ጓደኛ ለማግኘት የምታደርገው ፍለጋ ምን ያህል አድካሚ ሊሆን እንደሚችል ገምት። ወንዱ የእሳት እራት ይህን የመሰለ ችግር አለበት። ይሁን እንጂ ይህ ውብ ሦስት አፅቄ ችግሩን የሚያቀሉለት አንዳንድ ተፈጥሯዊ ባሕርያት አሉት።

ወደፊት ተጓዳኝ ፍለጋ የሚሠማራው ይህ የእሳት እራት በበጋ ወራት ገና በአባ ጨጓሬነት ደረጃ ላይ እያለ በደንብ አድርጎ ይመገባል። ለቀሪው የሕይወት ዘመኑ ማለትም ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት የሚያቆየውን ምግብ አከማችቶ በጸደይ ወራት የሙሽሬነት የዕድገት ደረጃውን ይጨርስና አንጸባራቂ የእሳት እራት ይሆናል።

የምግብ ችግሩ የተቃለለለት በመሆኑ አሁን ተጓዳኝ በመፈለጉ ሥራ ላይ ብቻ ሊያተኩር ይችላል። ሆኖም አንድ ጠቃሚ የሆነ መሣሪያ ባይኖረው ኖሮ አንዲትን ሴት የእሳት እራት በጨረቃ ብርሃን መፈለግ ማለት በተከመረ ገለባ ውስጥ የወደቀን መርፌ እንደ መፈለግ ይሆንበት ነበር።

በትንሹ የእሳት እራት ጭንቅላት ላይ እንደ ሳር የበቀሉ ሁለት አንቴናዎች ይገኛሉ። እነዚህ ትናንሽ አንቴናዎች በምድር ላይ አሉ ከሚባሉ መዓዛ የሚለዩ መሣሪያዎች ሁሉ ይበልጥ ውስብስብ ሳይሆኑ አይቀሩም። ከዚህም በላይ ሴቷ የእሳት እራት ሆን ብላ የምታወጣውን ጠረን ወይም የምትረጨውን “ሽቶ” የሚያነፈንፉ ናቸው።

የሴቶቹ ቁጥር አነስተኛ ሊሆን ቢችልም እንኳ ኃይለኛ የሆነው ጠረናቸው እንደ ጠቋሚ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል። የወንዶቹ የእሳት እራት አንቴናዎች በጣም ኃይለኛ በመሆናቸው አሥራ አንድ ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቃ የምትገኝን ሴት የእሳት እራት ለይተው ማወቅ ይችላሉ። በዚህ መንገድ መሰናክሎቹ ሁሉ ይወገዱና ወንዱ የእሳት እራት የሴት ጓደኛውን ያገኛል። ቢያንስ በዚህ ሁኔታ ፍቅር በሦስት አፅቄዎች ዓለም ውስጥ እውር ነው ሊባል ይችላል።

የአምላክ ፍጥረት እነዚህን በመሰሉ ማራኪና አስገራሚ በሆኑ ንድፎች የተሞላ ነው! መዝሙራዊው “አቤቱ፣ ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፤ ሁሉን በጥበብ አደረግህ” በማለት ጽፏል።​—⁠መዝሙር 104:​24

[በገጽ 26 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

© A. R. Pittaway