በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚያቀርብበት መንገድ ያስደስተኛል”

“የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚያቀርብበት መንገድ ያስደስተኛል”

“የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚያቀርብበት መንገድ ያስደስተኛል”

ንቁ! መጽሔት ለተለያዩ ርዕሶች ማብራሪያ የሚሰጥበትን መንገድ አስመልክቶ ይህን የተናገረው በዩካታን ሜክሲኮ የሚኖር አንድ ወጣት የንግድ አስተዳደር ረዳት ኃላፊ ነው። ይህ ሰው ንቁ! መጽሔት ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘው በሚሠራበት የመድህን ድርጅት ውስጥ የሥራ ባልደረባው ከሆነች የይሖዋ ምሥክር እንደሆነ በደብዳቤው ላይ ጠቅሷል።

ንቁ! መጽሔትን አስመልክቶ የሚከተለውን ጽፏል:- “በእርግጥም የእውቀትና የእውነት ምንጭ ነው። በፖለቲካ ጉዳዮች ጣልቃ ሳይገባና ሰዎችን ከሰዎች ሳያበላልጥ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚያቀርብበት መንገድ ያስደስተኛል። ይህን መጽሔት በማንበብ ለተለያዩ ችግሮች መፍትሔ አግኝቻለሁ። ይህ ማራኪ፣ ሚዛናዊ፣ ወቅታዊና እውቀት የሚጨምር መጽሔት ነው። ልባዊ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ!”

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ንቁ! መጽሔት የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት የሚያስከትለውን ከባድ ሃዘን ስለመቋቋም የሚያወሳ ርዕስ አውጥቶ ነበር። ያ መረጃ ከጊዜ በኋላ እንደገና ተዘጋጅቶ የምትወዱት ሰው ሲሞት በሚባለው ብሮሹር ላይ ወጣ። ምናልባት አንተም ሆንክ አንተ የምታውቀው ሌላ ሰው ይህን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር አንብባችሁ መጽናናት አግኝታችሁ ይሆናል። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተህ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ብሮሹር ማግኘት ትችላለህ።

የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ። በየትኛው ቋንቋ እንደምትፈልግ ጥቀስ

□ ያለ ክፍያ የሚደረገውን የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በተመለከተ እንድታነጋግሩኝ እፈልጋለሁ።