በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ለእናንተ ያለኝን ጥልቅ አድናቆት እገልጻለሁ”

“ለእናንተ ያለኝን ጥልቅ አድናቆት እገልጻለሁ”

“ለእናንተ ያለኝን ጥልቅ አድናቆት እገልጻለሁ”

የይሖዋ ምሥክሮች ስለሚያሳትሟቸው ጽሑፎችና ጽሑፎቹን እቤቱ ስለሚያደርሱለት ሰዎች ይህን አስተያየት የጻፈው ፌይርሆፕ፣ አላባማ ዩ ኤስ ኤ የሚኖር አንድ አጥባቂ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ነው።

እንዲህ ብሏል:- “የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች የአጻጻፍ ስልትና የሚያወጧቸው ርዕሶች በጣም የሚደነቁ ናቸው። የእናንተ ሰዎች እነዚህን መጽሔቶች ይዘውልኝ ሲመጡ ደስ ይለኛል። ሁለቱንም መጽሔቶች አነብ ባለሁ።

“የእናንተ ሰዎች በጣም ጥሩዎችና ጨዋዎች ስለሆኑ የአምላክን (የይሖዋን) ሥራ በደስተኝነት መንፈስ ሲሠሩ ማየት በጣም ያስደስተኛል። ባለፈው ጊዜ ሁለት ትንንሽ ልጆች ቤቴ መጡና ስማቸውን ካስተዋወቁኝ በኋላ መጽሔቶቹን አበረከቱልኝ። ትንንሽ ልጆች ከረብሻ ይልቅ ጥሩ ሥራ ሲያከናውኑ በማየቴ ስለተደሰትኩ አመሰገንኳቸው።

“እኔ አጥባቂ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ነኝ። . . . ሆኖም ድርጅታችሁና ሰዎቻችሁ እየሠሩ ያለውን ጥሩ ሥራ አደንቃለሁ። ከልብ ነው የምላችሁ መጽሔቶቻችሁን ማንበብ እወዳለሁ፤ እንዲሁም ግሩምና ፈገግታ የማይለያቸው ሰዎቻችሁን አደንቃለሁ። . . . ለእናንተ ያለኝን ጥልቅ አድናቆት እገልጻለሁ። መልካም ሥራችሁን ግፉበት።”

በተጨማሪም የይሖዋ ምሥክሮች የተለያዩ ርዕሶችን የሚያብራሩ ጽሑፎችን ያዘጋጃሉ። ከእነዚህ አንዱ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተሰኘው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ነው። በያዛቸው 16 ትምህርቶች ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ትምህርቶችና የአምላክን ሞገስ ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈረውን ያስተምረናል። የራስዎ ቅጂ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተሰኘውን ብሮሹር ማግኘት እፈልጋለሁ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።