በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“አቻ የማይገኝለት መጽሔት”

“አቻ የማይገኝለት መጽሔት”

“አቻ የማይገኝለት መጽሔት”

የንቁ! መጽሔት አዘጋጆች በቅርቡ በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር አንዲት የ18 ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የላከችው ደብዳቤ ደርሷቸው ነበር። እንዲህ ስትል ጻፈች:-

“በኮሌጅ ከሚሰጥ ትምህርት ጋር የሚመጣጠን አንድ የታሪክ ትምህርት ኮርስ ለመውሰድ ተመዘገብኩ። ከፍተኛ ጥናት የተደረገበት የጽሑፍ ሥራ ማቅረብ ያስፈልግ ስለነበር በናዚ አገዛዝ ዘመን የይሖዋ ምሥክሮች በጀርመን ስላሳዩት የሥነ ምግባር ጥንካሬ የሚገልጽ ጽሑፍ ለማዘጋጀት መረጥኩ። ስለዚህ በሐምሌ 8, 1998 የንቁ! መጽሔት እትም ላይ በወጣው ‘የይሖዋ ምሥክሮች​—⁠በናዚ ፊት ያሳዩት ድፍረት’ በሚለው ርዕሰ ትምህርት መደምደሚያ ላይ የተጠቀሰውን ተጨማሪ መረጃ የሚገኙባቸውን ጽሑፎች ዝርዝር እንድትልኩልኝ እጠይቃችኋለሁ። ጽሑፉ ከፍተኛ ጥናት የተደረገበትና አሳማኝ በሆነ መንገድ የቀረበ በመሆኑ በጽሑፉ ላይ ከተንጸባረቀው ጠንካራ ስሜትና እውነታ ከፊሉን እንኳ ወስጄ የጽሑፍ ሥራዬን ባዘጋጅ ሥራዬን ለሚገመግሙት ከፍተኛ ምሥክርነት ይሰጣል።

“እንዲህ ያለውን አቻ የማይገኝለት መጽሔት ያለማቋረጥ የምታዘጋጁ በመሆናችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። በእያንዳንዱ እትም ላይ በትምህርት ቤት ላገኘው ከምችለው የላቀ ‘የሥነ ጽሑፍ ትምህርት’ አገኛለሁ። ይህም በእያንዳንዱ በማዘጋጀው የሥነ ጽሑፍ ሥራዬ ማሻሻያ ለማድረግ እንድጣጣር አነሳስቶኛል። ጥረታችሁን የማደንቅ መሆኔን ልገልጽላችሁ እወዳለሁ።”

[በገጽ 18 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

መሃል ላይ ያለው ፎቶ:- Państwowe Muzeum Oświęcim-Brzezinka, courtesy of the USHMM Photo Archives