በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሥነ ምግባር ያዘቀጠው ለምንድን ነው?

ሥነ ምግባር ያዘቀጠው ለምንድን ነው?

ሥነ ምግባር ያዘቀጠው ለምንድን ነው?

ባለፈው ጥቅምት ወር በኢኳዶር ሎሃ የሚኖር አንድ ጋዜጠኛ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚያከናውኑት አገልግሎት የተሰማውን አድናቆት ገልጿል። ከሰጠው አስተያየት ውስጥ ቀጥሎ ያለው ይገኝበታል:-

“የሰውን ዘር እያጠቁ ካሉት አስከፊ መቅሰፍቶች አንዱ የሥነ ምግባር ማዝቀጥ ነው . . . ሰዎች አሥርቱን ትእዛዛት መጠበቅ የተዉና ሕሊናቸውን የጣሱ ይመስላል። ይህ ደግሞ በሰዎች መካከል አለመግባባት እንዲፈጠር ያደርጋል። በየትኛውም ቦታና በማንኛውም ጊዜ ስለ ጥላቻ፣ ዓመፅ፣ ወንጀል፣ የአደገኛ ዕፅ ዝውውር፣ ሽብርተኝነትና የሰውን ክብር ስለመግፈፍ ሲወራ እንሰማለን። . . .

“የይሖዋ ምሥክሮች ምንም ዓይነት ግርግር ሳይፈጥሩ ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ ጎረቤቶቻቸውን በማነጋገርና በጣም ግሩም ርዕሶች ይዘው የሚወጡትን መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! የተባሉ ማራኪ መጽሔቶቻቸውን በማሰራጨት ሥራቸውን ሰላማዊ በሆነና እርጋታ ባለው መንገድ ያከናውናሉ። በተለይ ደግሞ ንቁ! በማስረጃ የተደገፉ ሳይንሳዊና ባህል ነክ የሆኑ ትኩረት የሚስቡ የተለያዩ ጉዳዮችን ይዳስሳል። እነዚህ ርዕሶች ግልጽ በሆነና ባልተዛባ መንገድ የሚዘጋጁ መሆናቸው አድናቆት ያሳድራል።”

በዛሬው ጊዜ ሥነ ምግባር እያዘቀጠ መሄዱ በግልጽ ይታያል። ሆኖም በዚህ መጽሔት ገጽ 4 ላይ “ንቁ! የሚታተምበት ምክንያት” በሚለው ክፍል ሥር እንደቀረበው ንቁ! “ከወቅታዊ ሁኔታዎች በስተጀርባ ያለውን እውነተኛ ትርጉም ያስረዳል።” አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የተባለው ብሮሹር ሰዎች እየደረሰባቸው ያለውን መከራ ከመግለጽ ባሻገር የሚናገረው ነገር አለው። ብሮሹሩ በሰዎች ላይ አስከፊ መዘዝ ያስከተለው የሥነ ምግባር ውድቀት ሊከሰት የቻለበትን ምክንያት ይናገራል። ከሁሉም በላይ በቅርቡ እፎይታ ሊገኝ የሚችልበትን መንገድ ይገልጻል።

ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ማጽናኛ የያዘው ይህ ባለ 32 ገጽ ብሮሹር እንዲላክልዎት መጠየቅ ይችላሉ።

አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ። በየትኛው ቋንቋ እንደሚፈልጉ ይጥቀሱ

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።