ተጠራጣሪ ቢሆንም እውነታውን ለማወቅ ይጥራል
ተጠራጣሪ ቢሆንም እውነታውን ለማወቅ ይጥራል
ስሎቬንያ ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ ላይ የተጠመቀ የሮማ ካቶሊክ ተከታይ መሆኑን የገለጸ አንድ ሰው እንዲህ በማለት ጠይቋል:- “እባካችሁ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ። ንቁ! መጽሔት በቋሚነት ቤቴ ድረስ እንዲመጣልኝ ማድረግ የምችለው እንዴት እንደሆነም ማወቅ እፈልጋለሁ።”
ሰውዬው እንዲህ በማለት አብራርቷል:- “እባካችሁ ሐሳቤን ተረዱልኝ። ሃይማኖትን በተመለከተ ተጠራጣሪ ሰው ነኝ። ሆኖም ንቁ! መጽሔት ሳነብብ በጣም ነው የተገረምኩት። ምክንያቱም መጽሔቱ ግልጽና ትምህርታዊ በሆነ መንገድ ማብራሪያ ይሰጣል እንጂ ቀኖናዊ አይደለም። ለምሳሌ ያህል ድሩሺኔ [ቤተሰብ] የተሰኘውን የሮማ ካቶሊክ ሳምንታዊ መጽሔት ተመልከቱ። ይህ መጽሔት ሰዎች ማንን መምረጥ እንዳለባቸው ማለትም ለጥቅማቸው የቆመው ማን እንደሆነና እንዳልሆነ በመንገር ቃል በቃል አእምሮአቸውን ያጥባል።”
ሰውዬው አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር ለመጠየቅ በንቁ! መጽሔት ጀርባ ላይ ያለውን ቅጽ ከመጠቀም ይልቅ ደብዳቤ መጻፍ የመረጠበትን ምክንያት ሲገልጽ “መጽሔቱን ማበላሸት አልፈለግሁም” ብሏል። “መጽሔቱን እንዳለ ማስቀመጥ ፈለግሁ!”
አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር 16 ክፍሎች አሉት። በዚህ ብሮሹር ላይ መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ተብራርተዋል። በተጨማሪም የአምላክን ሞገስ ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን የሚያሳይ ሐሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቀርቧል። እርስዎም የዚህን ብሮሹር አንድ ቅጂ ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይላኩ።
□ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።
[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
በ240 ቋንቋዎች 113 ሚልዮን ቅጂዎች