በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለሁሉም ሰው የሚሆን “ወቅታዊ ምክር”

ለሁሉም ሰው የሚሆን “ወቅታዊ ምክር”

ለሁሉም ሰው የሚሆን “ወቅታዊ ምክር”

ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ያነበቡ አንዲት ሴት “በጣም ግሩምና ወቅታዊ የሆነውን ምክር ሳነብ ዓይኖቼ እንባ አቀረሩ” ሲሉ ጽፈዋል። “በቤተሰብ ውስጥ ሊፈጠር ለሚችለው ለእያንዳንዱ ፈታኝ ሁኔታ የሰዎችን ስሜት በጠበቀ መልኩ (በንድፈ ሐሳብ ደረጃ) የሚሰጠው ዝርዝር ሐሳብ ልቤን በእጅጉ የነካው ከመሆኑም በላይ በአድናቆት እንድዋጥ አድርጎኛል። . . . ምዕራፍ 8 ላይ ከደረስኩ በኋላ ንባቤን አቋርጬ ልጽፍላችሁ ተነሳሁ። ከዚህ በላይ መታገስ አልቻልኩም።”

በሰሜን ካሮላይና፣ ዩ ኤስ ኤ የሚኖሩት እኚህ አድናቆት ያደረባቸው አንባቢ “ቤተሰቤም ሆነ በምድር ዙሪያ የሚገኙ ሌሎች በርካታ ሰዎች በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ለሰፈሩት ሐሳቦች ከወትሮው የላቀ ትኩረት እንዲሰጡ ጸሎቴ ነው” ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

በምድር ዙሪያ የሚኖሩ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች 192 ገጾች ባሉት በዚህ ጽሑፍ በእጅጉ ተጠቅመዋል። ለሁሉም የቤተሰብ አባል ማለትም ለባል፣ ለሚስት፣ ለወላጆች፣ ለልጆችም ሆነ ለአያቶች የሚሆኑ ሐሳቦች የያዘ መጽሐፍ ነው። ትምህርት ሰጪ ከሆኑት ምዕራፎቹ መካከል “ልጆቻችሁን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ አሠልጥኗቸው፣” “በጉርምስና ዕድሜ የሚገኙ ልጆቻችሁ በጥሩ ሁኔታ እንዲያድጉ እርዷቸው፣” “ቤተሰባችሁን ጎጂ ከሆኑ ተጽዕኖዎች ጠብቁ” እንዲሁም “በቤተሰባችሁ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን አድርጉ” የሚሉት ይገኙባቸዋል።

የግል ቅጂ ማግኘት ይችሉ ዘንድ እባክዎ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይላኩ። የሚያጋጥሙዎትን ችግሮች ለመፍታት ሊረዱ የሚችሉና ፈጣሪያችን አቅዶት እንደነበረው የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ሊያደርጉ የሚችሉ ቀጥተኛ ሐሳቦች ያገኛሉ።

ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።