በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በጤና ችግር ተተብትበህ በምትያዝበት ጊዜ

በጤና ችግር ተተብትበህ በምትያዝበት ጊዜ

በጤና ችግር ተተብትበህ በምትያዝበት ጊዜ

“በትልቅ መዶሻ እንደተመታሁ ሆኖ ተሰማኝ።”—ጆን፣ ለአካል ጉዳት የሚዳርግ ሕመም እንደያዘው ካወቀ በኋላ የተናገረው።

“በጣም ፈራሁ።”—ቤት፣ ያጋጠማት የጤንነት እክል ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ከተገነዘበች በኋላ የተናገረችው።

በሕይወት ውስጥ ሊከሰቱ ከሚችሉት አስከፊ ገጠመኞች አንዱ ሥር የሰደደና ለአካል ጉዳት የሚዳርግ በሽታ ወይም በአካልህ ላይ ዘላቂ ጉዳት የሚያስከትል አደጋ ነው። ስለ አካላዊ እክልህ ያወቅኸው ጸጥታ በሰፈነበት የሐኪም ቢሮ ውስጥ ይሁን ወይም ትርምስ በበዛበት የድንገተኛ አደጋ ሕክምና ክፍል ውስጥ የደረሰብህን ሁኔታ ለማመን ሳያዳግትህ አይቀርም። መላ ሕይወትህ ከባድ በሆነ የጤና እክል በሚናጋበት ጊዜ አንቆ የሚይዝህን የስሜት መቃወስ መቋቋም በጣም ከባድ ነው።

ንቁ! በቅርቡ ከባድ የጤና እክል የገጠማቸውን ግለሰቦች ሊረዳ የሚችል መረጃ ለማሰባሰብ ሲል ለበርካታ ዓመታት ለአካል ጉዳተኛነት የዳረጋቸውን ሕመም ተቋቁሞ በመኖር ረገድ የተሳካላቸውን በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ የተለያዩ ግለሰቦች አነጋግሯል። እነዚህ ሰዎች ምን ዓይነት ስሜት ተሰምቶህ ነበር? ያጋጠመህን ከባድ ችግር እንድትቋቋምና ሚዛንህን እንድትጠብቅ የረዳህ ምን ነበር? እንደሚሉት ላሉ ጥያቄዎች አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ተጠይቀዋል። በአሁኑ ጊዜ የጤና እክል ያጋጠማቸውን ሰዎች ይረዳል በሚል እምነት ከእነዚህ ቃለ ምልልሶች የተቃረሙ ነጥቦችና ረዥም ዕድሜ ያላቸው ሕመሞች በሚያስከትሉት ውጤት ላይ ጥናት ያደረጉ ምሁራን የደረሱባቸው አንዳንድ ግኝቶች ቀርበዋል። *

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.5 ይህ ተከታታይ ጽሑፍ በተለይ የሚያተኩረው በታመሙ ወይም የአካል ጉዳተኞች በሆኑ ሰዎች ላይ ሲሆን “ሥር የሰደደ በሽታ​—⁠ችግሩን ለመቋቋም ቤተሰብ የሚጫወተው ሚና” (ንቁ! መስከረም 2000) በሚለው ርዕስ ሕመምተኞቹን ለሚያስታምሙ ቤተሰቦች የሚጠቅሙ መረጃዎች ቀርበዋል።