በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሰዎች ፈታኝ ሁኔታዎችን እንዲቋቋሙ መርዳት

ሰዎች ፈታኝ ሁኔታዎችን እንዲቋቋሙ መርዳት

ሰዎች ፈታኝ ሁኔታዎችን እንዲቋቋሙ መርዳት

በስሪላንካ የሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ በምሥራቃዊ የአገሪቱ ክፍል ከሚገኘው የወጣቶችና የሰው ኃይል ማደራጃ ቢሮ ጸሐፊ ደብዳቤ ደርሶት ነበር። ጸሐፊው የቆዩ የንቁ! መጽሔት እትሞች እንዲላኩላቸው ከጠየቁ በኋላ ስለ መጽሔቶቹ ያስተዋሉትን እንዲህ በማለት ጽፈዋል:-

“እኔና የሥራ ባልደረቦቼ የላካችሁልንን መጽሔቶች ትምህርት ሰጪ፣ አዲስ ነገር የሚያሳውቁና ቀስቃሽ እንዲሁም ምክንያታዊና አሳማኝ ሆነው አግኝተናቸዋል። አንዳንዶች በስህተት እንደሚያስቡት መጽሔቶቹ ስውር በሆነ መንገድ ክርስቲያናዊ መሠረተ ትምህርቶችን የሚያስፋፉ አይደሉም። ድንቅ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ሆነው አግኝቻቸዋለሁ።

“ቆየት ላሉትም ሆነ ለአዳዲሶቹ የንቁ! መጽሔት እትሞች ያለው ፍላጎት እየጨመረ የመጣ ሲሆን በቀጣዮቹ ወራትም ይበልጥ እንደሚጨምር የሚያሳይ ፍንጭ አለ። በመጽሔቶቻችሁ ላይ የሚወጡት ርዕሶች በዕድሜ ለገፉ፣ ለወጣቶች እንዲሁም ለልጆች የሚሆኑ ትምህርቶች የያዙ ናቸው። በዘመናችን ያሉትንም ሆነ ወደፊት የሚነሱትን ከዓለማዊ አስተሳሰብ የሚመነጩ ፈታኝ ሁኔታዎች ለመቋቋም ይረዳሉ።”

በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች የዛሬውን ያህል ለፈተናዎች የተጋለጡበት የታሪክ ወቅት ኖሮ አያውቅም። በተለይም ብዙዎች የወደፊቱ ጊዜ ምን ይዞልን ይሆን? እንዲሁም ስለ እኛ የሚያስብ ፈጣሪ ይኖር ይሆን? በማለት ያስባሉ። እንዲህ ያሉት ጥያቄዎች አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? በሚለው ብሮሹር ላይ አጥጋቢ በሆነ መንገድ መልስ አግኝተዋል። እርስዎም የዚህን ብሮሹር አንድ ቅጂ ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይላኩ።

አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።