በመጽሔቶቹ ሐቀኝነት ተደነቁ
በመጽሔቶቹ ሐቀኝነት ተደነቁ
አንድ በስፔይን የሚኖሩ የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር በአገራቸው ለሚገኘው የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ቅርንጫፍ ቢሮ ለንቁ! መጽሔት ያላቸውን አድናቆት የሚገልጽ ደብዳቤ ጽፈው ነበር። እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል:-
“በቅርቡ ንቁ! የተባለው መጽሔታችሁ ሁለት ቅጂዎች ደርሰውኛል። መጽሔቶቹ በተለያዩ ርዕሶች ላይ ያተኮሩ በጣም አስደሳች ቁም ነገሮችን እንደያዙ ተገንዝቤአለሁ። የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ አይደለሁም። ሆኖም የመጽሔቶቹን ሐቀኝነት አድንቄአለሁ። መጽሔቶቹ እጹብ ድንቅ የሆኑ ሥዕላዊ መግለጫዎች ያሏቸው ሲሆኑ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚሰጡት ማብራሪያ ከአድልዎ ነጻ የሆነና ሳይንሳዊ ነው። ላደረጋችሁት ጥረት ከልብ አመሰግናችኋለሁ።”
ንቁ! መጽሔት በብዙ ርዕሶቹ ውስጥ አንባቢዎቹ ትክክለኛ ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ የሚረዱ ከተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች የተውጣጡ መረጃዎች ያቀርባል። እንዲህ ያለው አቀራረብ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? በሚለው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ላይም ተንጸባርቋል። ለምሳሌ፣ “ሕይወት የተገኘው በአጋጣሚ ነውን?” በሚለውና “አንድ ንድፍ የራሱ ንድፍ አውጪ ያስፈልገዋል” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር የተብራሩት ከጉዳዩ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ነጥቦች በከዋክብት ምርምር፣ በማይክሮባዮሎጂ እንዲሁም በፊዚክስ የትምህርት መስኮች ከፍተኛ እውቀት በማካበት እውቅና ያገኙ ግለሰቦች ከሰጧቸው አስተያየቶች የተወሰዱ ናቸው።
እርስዎም ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? የሚለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ማግኘት ይችላሉ።
□ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።
[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕሎቹ ምንጮች]
ጋላክሲ:- Courtesy of Anglo-Australian Observatory, photograph by David Malin