በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“የምድር ሕዝብ ቁጥር ማሻቀብ”—መፍትሄ ይኖረው ይሆን?

“የምድር ሕዝብ ቁጥር ማሻቀብ”—መፍትሄ ይኖረው ይሆን?

“የምድር ሕዝብ ቁጥር ማሻቀብ”—መፍትሄ ይኖረው ይሆን?

በ1960 የዓለም ሕዝብ ቁጥር ሦስት ቢልዮን ደርሶ ነበር። በ2000 ደግሞ ይህ ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል። ካናዳ ውስጥ የሚታተመው ቫንኩቨር ሳን የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ “የዓለም ሕዝብ ቁጥር በእያንዳንዱ ሴኮንድ በሚወለዱ አምስት ሕፃናት አማካይነት በማሻቀብ ላይ ነው።” በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ከ10 ሚልዮን የሚበልጡ ነዋሪዎች ያሏቸው 23 ትልልቅ ከተሞች የሚገኙ ሲሆን በ2025 የዓለም ሕዝብ ቁጥር 10 ቢልዮን ይደርሳል ተብሎ ይገመታል!

ሳይንቲስቶች ይህ ሁኔታ ቋፍ ላይ በሚገኘው ሥርዓተ ምህዳር (ecosystem) ላይ ሊያስከትል የሚችለው ጫና እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። እያንዳንዱ አዲስ የምድር ዜጋ ምግብ፣ ውኃና መጠለያ ያስፈልገዋል። የሕዝብ ቁጥር እያደገ በሄደ መጠን የምግብ ፍጆታውና የሚወገደው ቆሻሻ መጠንም የዚያኑ ያክል ይጨምራል። የትልልቅ ከተሞችን እድገት መግታት አለመቻሉ ደግሞ ሁኔታውን ይበልጥ ተፈታታኝ ያደርገዋል። በሳን ዘገባ መሠረት ትልልቆቹ ከተሞች ‘በዙሪያቸው ከሚገኙት ገጠራማ ክልሎች የተለያዩ ጥሬ ሃብቶችን በማስገባት ከፍተኛ መጠን ያላቸውን መርዛማ ቆሻሻዎች መልሰው ያስወጣሉ።’

“የምድር ሕዝብ ቁጥር ማሻቀብ” መፍትሔ ይኖረው ይሆን? ደስ የሚለው፣ መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ በሰው ልጆች ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ እንደሚገባ ይገልጻል። አምላክ ይህንን የሚያደርገው እንዴት እንደሆነና ውጤቱ ምን እንደሚሆን ማወቅ ትችል ዘንድ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለውን መጽሐፍ አንብብ። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተህ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ መጽሐፉን ማግኘት ትችላለህ።

ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።