በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጤና ለሁሉም ሊደረስበት የሚችል ግብ ነውን?

ጤና ለሁሉም ሊደረስበት የሚችል ግብ ነውን?

ጤና ለሁሉም ሊደረስበት የሚችል ግብ ነውን?

አንተም ሆንክ ቤተሰብህ የተሻለ ጤና እንዲኖራችሁ ትመኛለህን? እንደምትመኝ የተረጋገጠ ነው። ይሁንና አብዛኞቻችን አልፎ አልፎ ብቻ ቀላል በሆኑ በሽታዎች የምንጠቃ ቢሆንም በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አቅም በሚያሳጣ የዕድሜ ልክ በሽታ ይሰቃያሉ።

ይሁን እንጂ ሕመምንና በሽታን ለመቀነስ መጠነ ሰፊ ጥረት በመካሄድ ላይ ነው። የተባበሩት መንግሥታት አካል የሆነውን የዓለም የጤና ድርጅትን (ደብሊው ኤች ኦ) እንደ ምሳሌ እንውሰድ። በ1978 የዓለም የጤና ድርጅት ባዘጋጀው ኮንፈረንስ ላይ ከ134 አገሮችና ከ67 የተመድ ድርጅቶች የተውጣጡ ልዑካን፣ ጤና እንዲሁ ከሕመም ወይም ከበሽታ መገላገል ማለት ብቻ እንዳልሆነ ተስማምተውበታል። ተሰብሳቢዎቹ እንዳሉት ከሆነ ጤና “የተሟላ አካላዊ፣ አእምሯዊና ማኅበራዊ ደኅንነት ማግኘት” ማለት ነው። አልፎ ተርፎም ልዑካኑ ጤና “መሠረታዊ የሆነ የሰው ልጅ መብት ነው” እስከ ማለት ደርሰዋል! በመሆኑም የዓለም የጤና ድርጅት “የዓለም ሕዝብ ሁሉ ጥሩ ጤና እንዲኖረው” ለማድረግ ግብ አውጥቷል።

ይህ ግብ የሚያስደስት ከመሆኑም በላይ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው። ይሁን እንጂ ይህ ግብ ሊደረስበት የመቻሉ አጋጣሚ ምን ያህል ነው? ትልቅ እምነት የሚጣልባቸው ሆነው ከተገኙትና ከፍተኛ አድናቆት ካተረፉት የሰው ልጅ የሥራ መስኮች አንዱ ሕክምና ነው። ዘ ዩሮፒያን የተሰኘው የብሪታንያ ጋዜጣ እንዳለው ከሆነ “ለአንድ በሽታ አንድ መድኃኒት የሚለው ‘ቅጽበታዊ ፈውስ’ የሚያስገኝ የሕክምና ጽንሰ ሐሳብ” በምዕራቡ ዓለም በሚኖሩ ሰዎች ዘንድ እየተለመደ መጥቷል። በሌላ አባባል የሕክምናው መስክ ለእያንዳንዱ ሕመም ቀላልና ቀጥተኛ የሆነ ፈውስ ያስገኛል ብለን እንጠብቃለን ማለት ነው። የሕክምናው መስክ ይህን ከፍተኛ ተስፋ መፈጸም ይችል ይሆን?