በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ልብ የሚነካ መልእክት ባለው ቪዲዮ በሚገባ መጠቀም

ልብ የሚነካ መልእክት ባለው ቪዲዮ በሚገባ መጠቀም

ልብ የሚነካ መልእክት ባለው ቪዲዮ በሚገባ መጠቀም

ቲሊ ገና የ12 ዓመት ልጅ ሳለች ትምህርት ቤት ውስጥ ለመመስከር የሚያስችላትን አጋጣሚ ተጠቅማለች። ስለ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በመማር ላይ እንዳሉ በጀርመን የተፈጸመው ታላቅ እልቂት ከዚህ ጋር ተያይዞ ተነሳ። በዚያ የመከራ ወቅት አይሁዳውያን ብቻ ሳይሆኑ የይሖዋ ምሥክሮችም ጭምር እንደተሰቃዩና እንደተገደሉ ቲሊ ለመምህሯ ነገረቻት። መምህሯም ቲሊ ፐርፕል ትራያንግልስ የተባለውን ቪዲዮ እንድታመጣ ፈቀደችላት። መምህሯ ቪዲዮውን ለክፍሉ ተማሪዎች ከማሳየቷ በፊት እንዲህ አለች:- “በእልቂቱ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አይሁዳውያን ተገድለው ስለነበር ሌሎች ስደት የደረሰባቸው ቡድኖች ተረስተው ነበር። ከእነዚህ መካከል የይሖዋ ምሥክሮች ይገኙበታል።”

መምህሯ በቪዲዮው በጣም ከመደነቋ የተነሣ ለተማሪዎቿ እንድታሳየው ለአንዲት ሌላ መምህር አዋሰቻት። ቲሊ የአራተኛ ክፍል መምህሯ ወንድም በእልቂቱ ወቅት በናዚዎች መገደሉ ትዝ ሲላት ቪዲዮውን ለመምህሩ ወሰደችለት። መምህሩም ቪዲዮውን በዚያው ምሽት ተመለከተው።

በአጠቃላይ ከ60 የሚበልጡ ሰዎች ፐርፕል ትራያንግልስ የተባለውን ቪዲዮ የተመለከቱ ሲሆን ቪዲዮው የብዙዎችን ፍላጎት ቀስቅሷል። ይህ ሁሉ የተገኘው አንዲት ትንሽ ልጅ ስለ እምነቷ ለመናገር ድፍረት በማሳየቷ ነበር።—መዝሙር 8:2