የሚወድዱትን ሰው በሞት ያጡ ሰዎችን የሚያጽናና
የሚወድዱትን ሰው በሞት ያጡ ሰዎችን የሚያጽናና
ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የይሖዋ ምሥክሮች፣ የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት የሚያስከትለውን ከባድ ሐዘን በተመለከተ አንድ ብሮሹር አውጥተው ነበር። በዩጎዝላቪያ ፌደራላዊ ሪፑብሊክ የሚኖር አንድ አንባቢ “ከልቤ ነው የምላችሁ የምትወዱት ሰው ሲሞት ስለተባለው ብሮሹር ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። በእርግጥም የሚወዱትን ሰው በሞት ስለማጣት ዝርዝር ሐሳብ ይዟል” በማለት በቅርቡ የአድናቆት ደብዳቤ ልኮ ነበር።
ጸሐፊው እንዲህ ብሏል:- “በመኪና አደጋ ወንድሜን በሞት ባጣሁ ጊዜ ከዚህ ብሮሹር ‘በወቅቱ በጣም ያስፈልገኝ የነበረውን ማጽናኛ’ አግኝቻለሁ። በገጽ 18 ላይ የሚገኘው ‘አንዳንድ ተግባራዊ ምክሮች’ የሚለው ክፍል እንድጽናና በጣም ረድቶኛል። ይሁን እንጂ ከአራት ወራት በኋላ የወንድሜ ናፍቆት ክፉኛ ያሰቃየኝ ጀመር። ስሜታዊ ጤንነቴ አደጋ ላይ ወድቋል የሚል ፍርሃት ነበረብኝ።
“ብሮሹሩን እንደገና አነበብኩትና በገጽ 9 ላይ ከሚገኘው ‘የሐዘን ሂደት’ ከሚለው ሣጥን ናፍቆት የታከለበት ሐዘን የሚመጣው በመረጋጊያ ጊዜ ላይ እንደሆነ ተገነዘብኩ። በእውነቱ በጣም ነበር የተጽናናሁት። ይህን ብሮሹር በማዘጋጀት ላሳያችሁን ከልብ የመነጨ ርኅራኄ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።”
ምናልባት አንተም ሆንክ የምታውቀው ሌላ ሰው ይህን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር አንብባችሁ መጽናናት አግኝታችሁ ይሆናል። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተህ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ብሮሹር ማግኘት ትችላለህ።
□ የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።