በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ልጆችን ማሳደግ የሚያስከትለው ተፈታታኝ ሁኔታ

ልጆችን ማሳደግ የሚያስከትለው ተፈታታኝ ሁኔታ

ልጆችን ማሳደግ የሚያስከትለው ተፈታታኝ ሁኔታ

ብሪታኒያ ከበለጸጉት ምዕራባውያን አገሮች መካከል አንዷ ናት። ሆኖም በየዓመቱ ከ100, 000 በላይ ሕፃናት ይኸውም ከዚህ ቀደም ከተገመተው ሁለት እጥፍ የሚያህሉ ሕፃናት ቤታቸውን ጥለው ይጠፋሉ። በዚህም ምክንያት ከሰባት ሕፃናት መካከል አንዱ ዓመፅ ወይም የጾታ ጥቃት ይፈጸምበታል።

ችልድረንስ ሶሳይቲ የተባለ ድርጅት ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ኢያን ስፓርክስ “ልጆች እንደተገለሉና እንደተጠሉ ሲሰማቸው መፍትሔው ከቤት መጥፋት ሊመስላቸው ይችላል” ብለዋል። አክለውም “ይህ ችግር ሃብታምና ድሃ ሳይል የሚከሰት ነው። በተንደላቀቁ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ልጆች እንደሚጠፉት ሁሉ በድኾች መንደር ውስጥ የሚኖሩትም ይጠፋሉ።”

ልጆችን ማሳደግና ማሰልጠን ከባድ ኃላፊነት ነው። ታዲያ እርዳታ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው? ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለው ጽሑፍ ለዚህ ሲባል የተዘጋጀ ነው። ከያዛቸው 16 ምዕራፎች መካከል:- “ልጆቻችሁን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ አሠልጥኗቸው፣” “በጉርምስና ዕድሜ የሚገኙ ልጆቻችሁ በጥሩ ሁኔታ እንዲያድጉ እርዷቸው፣” እንዲሁም “ቤተሰብን የሚያናጉ ችግሮችን መቋቋም ትችላላችሁ” የሚሉት ይገኙበታል። መጽሐፉ የያዛቸው 16 ምዕራፎች በሙሉ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ምክሮችን ያዘለ ሲሆን ከሁሉም በላይ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን እኛ ካለን የሚልቅ የጥበብ መፍለቂያ አድርጎ ይጠቀምበታል።

ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለበለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ማግኘት ይችላሉ።

ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።