በሚያስፈልገኝ ጊዜ የወጣ ጽሑፍ
በሚያስፈልገኝ ጊዜ የወጣ ጽሑፍ
በኪዩቤክ ካናዳ የምትኖረው ግሎሪያ “ሰኔ 8, 2000 ንቁ! * መጽሔት እትም ላይ ላወጣችሁት ‘ከዓይንህ ፊት የሚንቀሳቀሱ ጉድፍ መሳይ ነገሮች አሉን?’ ለሚለው ርዕስ በጣም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ” በማለት ጽፋለች። “ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በዓይኔ ፊት ጥቃቅን ጉድፍ መሳይ ነገሮች ማየት የጀመርኩ ሲሆን ሰዎች የተለመደ እንደሆነ ነገሩኝ። በቅርቡ ግን የእነዚህ ጉድፍ መሳይ ነገሮች መጠን እየጨመረ ስለመጣ ሁኔታው ያሳስበኝ ጀመር።
“ጽሑፉ፣ የሚታዩህ ጉድፍ መሳይ ነገሮች ቁጥራቸው እየጨመረ ከመጣ ዓይንህን መመርመሩ ጥሩ ነው ይላል። እኔም ያደረግሁት ይህንኑ ነው። ወደ አንድ የዓይን ሐኪም ሄጄ ስመረመር ረቲናዬ የተቀደደ ቦታ እንዳለው ነገረኝ። ዶክተሩ መለስተኛ ቀዶ ሕክምና እንደሚያስፈልገኝ ከገለጸልኝ በኋላ ስለ አሠራሩ ሊያስረዳኝ ሞከረ። በንቁ! መጽሔት ገጽ 24 ላይ የሚገኘውን የዓይን ሥዕል አሳየሁት። ሥዕሉን ተጠቅሞ ሁኔታውን ካብራራልኝ በኋላ ሽፋኑን ተመለከተና ‘ንቁ! ነው እንዴ ለካ’ ብሎ መጽሔቱን ፋይሉ ውስጥ አስቀመጠው።
“ቀዶ ሕክምናው ስኬታማ የነበረ ሲሆን እኔም በጣም ተደስቻለሁ። ለንቁ! መጽሔት ምስጋና ይግባውና ረቲናዬ መቀደዱን ቶሎ ባልደርስበት ኖሮ ይብሱኑ በቀላሉ ከቦታው ይላቀቅ ነበር።”
ንቁ! የሕክምና መጽሔት ባይሆንም ብዙውን ጊዜ ጤናን እና ሕክምናን አስመልክቶ እውቀት ሰጪ ዘገባዎችን ይዞ ይወጣል። የሰው ልጆች አካል ፈጣሪ የተሻለ የሚባልለት የሕክምና ዘዴ ሊያስገኝ የማይችለውን ፍጹም ጤንነት ለመስጠት ቃል ገብቷል። የሰውን ዘር የመፈወስ ዓላማውን የሚፈጽመው እንዴት ነው? የገባውን ቃል እንደሚፈጽም እምነት ሊጣልበት ይችላልን?
የእነዚህንና የሌሎች ጥያቄዎች መልስ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? በተባለው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ውስጥ ማግኘት ትችላለህ። በተለይም “አምላክ የሚያመጣው ግሩም የሆነ አዲስ ዓለም” በሚል ርዕስ ክፍል 10 ሥር ያለውን ሐሳብ ማንበብ ሳያስደስትህ አይቀርም። ይህን ብሮሹር ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተህ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ትችላለህ።
□ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።
[የግርጌ ማስታወሻ]
^ አን.2 በአማርኛ ንቁ! ሰኔ 2000 ገጽ 11 ላይ ይገኛል።