በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ልጆች ተግሳጽ ሊሰጣቸው የሚገባው እንዴት ነው?

ልጆች ተግሳጽ ሊሰጣቸው የሚገባው እንዴት ነው?

ልጆች ተግሳጽ ሊሰጣቸው የሚገባው እንዴት ነው?

“ልጆች ምንም ያድርጉ ምን የሚሞካሹ ከሆነ ችግር ይፈጠራል” ይላል የካናዳው ናሽናል ፖስት ጋዜጣ። አንዳንድ ወላጆች እንዲህ ማድረግ የልጆቻቸውን በራስ የመተማመን መንፈስ እንደሚያጎለብተው ያምናሉ። ይሁን እንጂ ሮይ ባውማይስተር የተባሉት የሥነ ልቦና ሐኪም እንደተናገሩት “ባገኙት ስኬት ላይ የተመሠረተ በራስ የመተማመን መንፈስ ተገቢ ቢሆንም ወላጆች ልጆቻቸው ራሳቸውን እንዲገዙ በማሰልጠን ላይም ሊያተኩሩ ይገባል።”

ልጁ ሲያጠፋ ለማረም የሚሳሳ ወላጅ ልጁን እየበደለው ነው። ደግሞም እርማት የማስተማሪያ ዘዴ ነው። በመሆኑም አንድ ጥፋት የሠራ ልጅ ያንን ስህተቱን እንዳይደግም ያስተምረዋል። እርግጥ ወላጆች ጭካኔ የተሞላበትና ከልጆች ጥፋት ጋር የማይመጣጠን እርማት መስጠት የለባቸውም። (ኤርምያስ 46:​28) የሚሰጡት እርማት ከልክ ያለፈ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ “አባቶች ሆይ፣ ልባቸው እንዳይዝል ልጆቻችሁን አታበሳጩአቸው” ይላል።​—⁠ቆላስይስ 3:21

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እርማት በተደጋጋሚ የተጠቀሰው ከቁጣና ከጭካኔ ጋር ሳይሆን ከፍቅርና ከየዋኅነት ጋር ተያይዞ ነው። ጥበበኛ የሆነ መካሪ “ለሰው ሁሉ ገር . . . ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም። ደግሞም . . . የሚቃወሙትን በየዋህነት [ይቀጣል]።” (2 ጢሞቴዎስ 2:24, 25) እንግዲያው ወላጆች የሚሰጡት እርማት የእልህ መወጫ ሊሆን አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ በልጁ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ቅጣትን በምንም ዓይነት አይደግፍም።

በምድር ዙሪያ የሚኖሩ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች 192 ገጾች ካሉት ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ከተባለው ጽሑፍ ተጠቅመዋል። ትምህርት ሰጪ ከሆኑት ምዕራፎቹ መካከል “ልጆቻችሁን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ አሰልጥኗቸው” እና “በጉርምስና ዕድሜ የሚገኙ ልጆቻችሁ በጥሩ ሁኔታ እንዲያድጉ እርዷቸው” የሚሉት ይገኙባቸዋል። የግል ቅጂ ማግኘት ይችሉ ዘንድ እባክዎ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያ ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይላኩ። የሚያጋጥሙዎትን ችግሮች ለመፍታት ሊረዱ የሚችሉና ፈጣሪያችን አቅዶት እንደነበረው የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ሊያደርጉ የሚችሉ ቀጥተኛ ሐሳቦች ያገኛሉ።

ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።