በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በሃይማኖቱ የሚኮራ ወጣት

በሃይማኖቱ የሚኮራ ወጣት

በሃይማኖቱ የሚኮራ ወጣት

አንድሩ በ13 ዓመት ዕድሜው ባህላዊ ቅርስ በሚል ርዕስ በትምህርት ቤቱ አንድ ፕሮጀክት እንዲያዘጋጅ ታዘዘ። “መጀመሪያ ላይ” ይላል አንድሩ “ስለ ወንድ አያቴ ልጽፍ አሰብኩ፤ ሆኖም ረጋ ብዬ ሳስብበት ‘እንዴ ቆይ እንጂ! እኔ እኮ የይሖዋ ምሥክር ነኝ። ይህ ስለ እምነቴ ለመናገር ግሩም አጋጣሚ ነው!’ አልኩ።”

“የፕሮጄክቴን ጭብጥ ‘ጸንቶ መቆም’ አልኩት። ከዚያም የይሖዋ ምሥክሮች በናዚ ጀርመን ያጋጠማቸውን አረመኔያዊ ስደት የሚያሳይ ትልቅ ፖስተር አዘጋጀሁ። ለእይታ ካቀረብኳቸው ነገሮች መካከል ራሴ አስመስዬ የሠራሁት ባለ ሦስት ማዕዘን ወይን ጠጅ ምልክት ያለበት የደንብ ልብስ እንዲሁም የኩሰሮ ቤተሰብ የተለያዩ ደብዳቤዎችና ስዕሎች ይገኙበታል። * የይሖዋ ምሥክሮች ለጀርመን መንግሥት የላኩትን ከፖለቲካ ገለልተኛ የሆነ መልእክት ያዘለ ሆኖም በይሖዋ ምሥክሮች ላይ የሚፈጸመውን ግፍ ፊት ለፊት የሚቃወም ደብዳቤ ቅጂ ለአድማጮቼ አደልኩ። ከፕሮጀክቱ ጎን ለጎን የይሖዋ ምሥክሮች የናዚን ጥቃት ተቋቁመዋል የተሰኘው የቪዲዮ ፊልም ይታይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱሶችን፣ ብሮሹሮችንና ትራክቶችንም ለእይታ አቅርቤ ነበር።

“መጀመሪያ ፕሮጀክታችንን ያቀረብነው ሁሉም ተማሪዎችና የትምህርት ቤቱ ሠራተኞች በተገኙበት በስፖርት ማዕከሉ ነበር። በቀጣዩ ምሽት ደግሞ ቤተሰቦችና ጓደኞች ተጋበዙ። ብዙዎች የይሖዋ ምሥክሮች በናዚዎች ስደት እንደደረሰባቸው ምንም የሚያውቁት ነገር ስለሌለ ጥያቄዎች ይጠይቁኝ ነበር።”

አንድሩ ስለ እምነቱ ለመናገር ድፍረት እንደጠየቀበት አልሸሸገም። “አንዳንድ ሰዎች እንደሚያሾፉብኝ አላጣሁትም፤ ሆኖም ይህን አጋጣሚ ስለ እምነቴ ለመናገር ባልጠቀምበት ኖሮ በጣም አዝን ነበር። በይሖዋ ላይ ያላቸውን እምነት ለመጠበቅ ሲሉ ሕይወታቸውን ስለሠዉ ሰዎች እየተናገርኩ እኔ ይህን ትችት መቋቋም ይበዛብኛል?” ሲል ተናግሯል።

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ አንድሩ አጋጣሚውን ምሥክርነት ለመስጠት ስለተጠቀመበት ተደስቶ ነበር። “ለምን ወደ ጦርነት እንደማንሄድ ጥያቄ ተነስቶ ብዙ ተወያይተናል። ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሶች፣ መጻሕፍትና ትራክቶች አበርክቻለሁ። የይሖዋ ምሥክር በመሆኔ የዛሬውን ያህል የኮራሁበት ጊዜ የለም” ሲል ተናግሯል።

[የግርጌ ማስታወሻዎች]

^ አን.3 የይሖዋ ምሥክሮች በእስር ቤቶቹ ውስጥ ተለይተው የሚታወቁት ወይን ጠጅ ቀለም ባለው ሦስት ማዕዘን ምልክት ነበር። የኩሰሮ ቤተሰብ በናዚ አገዛዝ ሥር የይሖዋ ምሥክሮች ሆነው በእምነታቸው ጸንተዋል። የመስከረም 1, 1985 መጠበቂያ ግንብ (እንግሊዝኛ) ገጽ 10-​15 ተመልከት።