በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የዓለም ሰላም ሕልም ብቻ ሆኖ አይቀርም!

የዓለም ሰላም ሕልም ብቻ ሆኖ አይቀርም!

የዓለም ሰላም ሕልም ብቻ ሆኖ አይቀርም!

አልፍሬድ ኖቤል ያለፈውን መቶ ዘመን መለስ ብሎ ለማየት ቢችል ኖሮ የዓለም ሰላም እንደሚመጣ ብሩሕ ተስፋ ይኖረው ነበር? ጦርነት ለማስቀረት ልባዊ ጥረት ያደረጉ በርካታ ሰዎች መኖራቸውን በማወቁ ደስ መሰኘቱ እንደማይቀር የታወቀ ነው። ይሁን እንጂ ካለው መራራ ሐቅ ጋር መፋጠጡ አይቀርም። ፕሮፌሰር ሃዩ ቶማስ ሁኔታውን ጠቅለል አድርገው እንዲህ በማለት አስቀምጠዋል:- “ሃያኛው መቶ ዘመን በአጠቃላይ ማኅበራዊ እድገት የታየበትና መንግሥታት ለድሆች ሕይወት የበለጠ አሳቢነት ያሳዩበት ዘመን ይሁን እንጂ መትረየስ፣ ታንክ፣ ቢ-52፣ ኑክሊየር ቦምብ፣ በመጨረሻም ሚሳይል የነገሠበት ዘመን ነበር። በማንኛውም ሌላ ዘመን ታይተው በማይታወቁ አውዳሚና ደም አፋሳሽ ጦርነቶች ተለይቶ የሚታወቅ ዘመን ሆኗል።” ቶማስ በማከል “ስለዚህ ይህን ዘመን የእድገት ዘመን ነውም፣ አይደለምም ለማለት ለእያንዳንዱ ሰው የተተወ ነው” በማለት አጠቃለዋል።

አሁን 21ኛው መቶ ዘመን ውስጥ ስለገባን የዓለም ሰላም የማስፈን ተስፋችን ይበልጥ አስተማማኝ ሆኗል? በፍጹም! ኒውስዊክ መጽሔት በኒው ዮርክና በዋሽንግተን ዲ ሲ ከተሞች ላይ መስከረም 11 ቀን 2001 የደረሰውን የአሸባሪዎች ጥቃት በተዘዋዋሪ መንገድ በመጥቀስ “767 ጄት አውሮፕላኖች የታለሙ ሚሳይሎች ሆነው ሊያገለግሉ በሚችሉበት ዓለም ውስጥ ሊሆን አይችልም፣ የማይመስል ነገር ነው፣ ወይም ከሁሉ የሚከፋው ደግሞ እንዳይደርስ ሊደረግ የሚችል ምንም ነገር የለም” ብሏል።

የዓለም ሰላም እውን እንዲሆን ከተፈለገ ሁለት ነገሮች መሟላት እንዳለባቸው አንዳንዶች ይናገራሉ። አንደኛ፣ በሰዎች አመለካከትና ባሕርይ ላይ ሥር ነቀል ለውጥ መካሄድ ይኖርበታል። ሁለተኛ፣ ሁሉም ብሔራት በአንድ መንግሥት ሥር መጠቃለል ይኖርባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ሰላም የሚሰፍንበት ጊዜ እንደሚመጣ ይተነብያል። ይህ ሰላም የሚመጣው ግን በሰው ልጆች ጥረት አይደለም። መዝሙር 46:​9 ስለ ፈጣሪያችን ስለ ይሖዋ አምላክ “እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነትን ይሽራል” ይላል። (በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።) አምላክ ይህን የሚያከናውነው እንዴት ነው? ብዙ ቅን ሰዎች በተደጋጋሚ ሲጸልዩለት በቆየው መንግሥት አማካኝነት ነው። ይህ መንግሥት አምላክ ከአንደኛው የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ ሰላም የሚያሰፍንበት እውነተኛ መስተዳድር ነው እንጂ ሊጨበጥ የማይችል የልብ ሁኔታ አይደለም። በመንፈስ አነሳሽነት ይተነብይ የነበረው ኢሳይያስ የዚህ መንግሥት ተገዢዎች “ጦርነትን ከእንግዲህ አይማሩም” ብሏል። (ኢሳይያስ 2:​4 አ.መ.ት ) ሰዎች ምድር አቀፍ በሆነ የትምህርት መርሐ ግብር እንዴት እርስ በርሳቸው በሰላም እንደሚኖሩ ይማራሉ። በዚህም መንገድ “ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ።”

አሁንም እንኳን የይሖዋ ምሥክሮች ይህን በማድረግ ላይ ናቸው። እያንዳንዳቸው የየራሳቸው ጎሣና ነገድ ቢኖራቸውና ከ200 በሚበልጡ የተለያዩ አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ቢሆኑም በሌላ ሰው ላይ የጦር መሣሪያ ለማንሳት ፈጽሞ እሺ አይሉም። ገለልተኛ አቋማቸው በጦርነት በሚታመስ ዓለም ውስጥ ሰላም ሊገኝ የሚችል እርግጠኛ ተስፋ እንጂ ሕልም ብቻ ሆኖ የሚቀር ተምኔታዊ ቅዠት አለመሆኑን ያረጋግጣል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለ ተመሠረተ ስለዚህ እውነተኛ የሰላም ተስፋ ይበልጥ ለማወቅ ትፈልጋለህ? በገጽ 5 ላይ ከተዘረዘሩት አድራሻዎች የሚቀርብህን በመጠቀም ለዚህ መጽሔት አዘጋጆች ደብዳቤ ጻፍ ወይም በአካባቢህ የሚገኙትን የይሖዋ ምሥክሮች አነጋግር።