በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለሚረብሸው ድምፅ የፈጠረችው ዘዴ

ለሚረብሸው ድምፅ የፈጠረችው ዘዴ

ለሚረብሸው ድምፅ የፈጠረችው ዘዴ

“የምሠራው በአንድ የአሻንጉሊት ማምረቻ ኩባንያ ውስጥ ነው። ሥራው በጣም ተደጋጋሚ ስለሆነ ሠራተኞቹ ሙዚቃ እንዲያዳምጡ ይፈቀድላቸዋል። አጠገቤ ባለው ክፍል ውስጥ የምትሠራው የሥራ ባልደረባዬ መጥፎ ሙዚቃዎችን ማዳመጥ ትወዳለች። እኔ ክፍል ውስጥ ያሉ ሌሎች ሁለት ሠራተኞችም ይህ ዓይነቱን ሙዚቃ መስማት ደስ ይላቸዋል። ለእኔ ግን ስምንት ሰዓት ሙሉ እንዲህ ያለውን ሙዚቃ ሲያዳምጡ መዋል ትልቅ ፈተና ነበር።

“ሥራውን እንዳልተው የማገኛቸው ብዙ ጥቅሞች አሉ። አንደኛ ነገር አለቃዬ በአውራጃና ለሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በሚዘጋጁ ልዩ ስብሰባዎች ላይ እንድገኝ ትፈቅድልኛለች። ከዚህም በላይ ሥራ ቦታዬ ለመድረስ ብዙ መጓዝ አያስፈልገኝም። የሥራ ፕሮግራሜም ቢሆን በአገልግሎት ለመካፈል ያስችለኛል።

“በመጨረሻም የሥራ ባልደረባዎቼን ለማነጋገር ወሰንኩና ወይ ሙዚቃውን እንዲለውጡ አሊያም ድምፁን እንዲቀንሱልኝ በትህትና ጠየቅኳቸው። እነርሱ ግን ወደ አለቃዬ ሄደው ከሰሱኝ። አለቃዬም ቢሮዋ አስጠራችኝና ‘ሻረን፣ ይህንን ኩባንያ ወደ አንቺ ሃይማኖት መለወጥ አትችይም። ሠራተኞቻችን የፈለጉትን ማዳመጥ ይችላሉ’ አለችኝ።

“በዚህ ጊዜ የራሴን ክርና የጆሮ ማዳመጫ ማምጣት ይፈቀድልኝ እንደሆነ ጠየቅኩ። አለቃዬም በጥያቄዬ ተስማማች። ከዚያም በቴፕ ክር የተቀዳ የመጠበቂያ ግንብ እትም አመጣሁ። እንዲህ ማድረጌ መጥፎ ሙዚቃ ከመስማት የገላገለኝ ከመሆኑም በተጨማሪ በመንፈሳዊ ጠንካራ እንድሆንም አስችሎኛል።”—ተጽፎ የተላከልን