በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቁጥሮች በሕይወትህ ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ አለን?

ቁጥሮች በሕይወትህ ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ አለን?

ቁጥሮች በሕይወትህ ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ አለን?

ቁጥሮች ስውር ትርጉም አላቸውን? አንዳንዶች “እንዴታ!” ብለው ይመልሳሉ። ለዚህም መስከረም 11, 2001 የደረሰውን የአሸባሪዎች ጥቃት በማስረጃነት ይጠቅሳሉ።

አንዲት መጽሐፍ ገላጭ “ወዲያው ዜናውን እንደሰማሁ ልብ ያልኩት ቀኑ 9-11-2001 መሆኑን ነው” ብለዋል። መጽሐፍ ገላጮች 11 ቁጥር “ልዩ ትርጉም” ካላቸው ቁጥሮች አንዱ ነው የሚል እምነት አላቸው። ስለዚህ ዐውደ ነገሥት የሚከታተሉ ሰዎች የአሸባሪዎቹ ጥቃት “ልዩ ትርጉም ካለው ” ከ11 ቁጥር ጋር የሚዛመድባቸውን የተለያዩ ሁኔታዎች ዘርዝረዋል። የደረሱባቸው ግኝቶች በከፊል የሚከተሉት ናቸው:-

■ አደጋው የደረሰው በ9/11 ነበር። . . . 9 + 1 + 1 = 11

■ መስከረም 11 የዓመቱ 254ኛ ቀን ነበር። . . . 2 + 5 + 4 = 11

■ የሰሜኑን ሕንጻ የመታው አውሮፕላን የበረራ ቁጥር 11 ነበር።

■ የዚህ አውሮፕላን ተሳፋሪዎች ብዛት 92 ነበር። . . . 9 + 2 = 11

■ የደቡቡን ሕንጻ በመታው አውሮፕላን ውስጥ 65 ተሳፋሪዎች ነበሩ። . . . 6 + 5 = 11

■ የመንትዮቹ ሕንጻዎች ቅርጽ 11 ቁጥር ይመስላል።

■ “ኒው ዮርክ ሲቲ” የሚለው ቃል በእንግሊዝኛ 11 ሆሄያት አሉት።

ለነጠላ ቁጥሮች፣ ለቁጥሮች ድምርና ቅንጅት የተለየ ትርጉም መስጠት በአፍሪካ፣ በእስያና በአሜሪካ አገሮች በጣም የተስፋፋ ልማድ ነው። ይህ ልማድ የብዙዎችን ትኩረት የሚስበው ለምንድን ነው? በኢንተርኔት ላይ የወጣ አንድ ዘገባ እንዳለው ከዚሁ ልማድ ጋር በተያያዘ መንገድ የስሞችን ሆሄያት ምሥጢራዊ ትርጉም መፍታት “ስለ አንድ ግለሰብ ባሕርይ፣ ተፈጥሮ፣ ጠባይና ደካማ ጎን ትክክለኛ መረጃ ያስገኛል።” ይኸው ዘገባ እንዳለው የተወለድንበትን ቀን ማጥናት “የሕይወታችንን ጎዳና እንዲሁም የሚያጋጥመንን አስደሳች ሁኔታና ፈተና እንድናውቅ ይረዳናል።”

ታዲያ እነዚህ አባባሎች ትክክል ናቸው? ወይስ የቁጥሮችን ምትሐታዊ ምሥጢር ማጥናት ስውር ለሆነ አደጋ ያጋልጠናል?