በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታውን ተቀበለ

ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታውን ተቀበለ

ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታውን ተቀበለ

በቅርብ ዓመታት የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በየዓመቱ ይቀርቡለት ከነበሩት 7, 000 አቤቱታዎች መካከል የጽሑፍ ብይን ለመስጠት የተቀበለው ከ80 እስከ 90 የሚያህሉትን ብቻ ሲሆን ይህም ከአንድ በመቶ ብዙም አይበልጥም ማለት ነው።

የይሖዋ ምሥክሮች በግንቦት ወር 2001 ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ታይቶ የጽሑፍ ብይን እንዲሰጣቸው የሚከተለውን አቤቱታ አቀረቡ:- “ለበርካታ መቶ ዓመታት ሲካሄድ የቆየውንና በቅዱሳን ጽሑፎች የታዘዘውን ከቤት ወደ ቤት እየተዘዋወሩ ሃይማኖታዊ እምነትን የማስፋፋት ሥራ ሕገ መንግሥቱን ሳይተላለፉ የሚያከናውኑት ሃይማኖታዊ አገልጋዮች እንደተራ ሸቃጮች ተቆጥረው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ለመናገር ወይም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን አለክፍያ ለማሰራጨት ከማዘጋጃ ቤት ፈቃድ እንዲያወጡ ማስገደድ ተገቢ ነው?”

ጥቅምት 15 ቀን 2001 የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኒው ዮርክ የሚገኘው የመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር በስትራተን መንደር ላይ ያቀረበውን አቤቱታ መቀበሉ ለመጠበቂያ ግንብ የሕግ ክፍል ተገለጸ።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያተኮረው የሕገ መንግሥቱ የመጀመሪያ ማሻሻያ የመናገር ነጻነት ያስገኘው ጥበቃ፣ ሰዎች የመንግሥት ባለሥልጣኖችን ፈቃድ ሳይጠይቁ ስለ እምነታቸው ለሌሎች የመናገር መብታቸውን ይጨምራል ወይስ አይጨምርም በሚለው ላይ ነበር።

ጉዳዩ በዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዘጠኝ ዳኞች ፊት የቃል ክርክር እንዲደረግበት ተወሰነ። ምሥክሮቹ ጠበቆቻቸውን ሲያቀርቡ የስትራተን መንደርም ተከላካይ ጠበቆቹን አቅርቧል። ታዲያ የክርክሩ ውጤት ምን ሆነ?

[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

የመጀመሪያው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ምንድን ነው?

“የመጀመሪያው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ (የሃይማኖትን፣ የመናገርን፣ እምነትን የማስፋፋትን፣ የመሰብሰብን፣ አቤቱታ የማቅረብን ነጻነት ለማረጋገጥ የወጣ):- ምክር ቤት አንድ ሃይማኖት እንዳይቋቋም፣ ወይም አንድን ሃይማኖት የመከተልን ነጻነት የሚገድብ ወይም የመናገርን፣ የመጻፍን፣ የሕዝቦችን በሰላም የመሰብሰብን መብት የሚከለክል፣ ወይም በደል ሲፈጸም ለመንግሥት አቤቱታ የማቅረብ መብትን የሚያግድ ሕግ ሊያወጣ አይችልም።”​​—⁠⁠የዩናይትድ ስቴትስ ሕገ መንግሥት

“በዩናይትድ ስቴትስ ለዲሞክራሲ ሂደት መነሻ የሆነው የመጀመሪያው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ነው። ይህ ማሻሻያ ምክር ቤት የመናገር፣ የመጻፍ፣ በሰላም የመሰብሰብ ወይም አቤቱታ የማቅረብ ነጻነት የሚገድብ ሕግ እንዳያወጣ ይከለክላል። ብዙ ሰዎች የመናገር ነጻነት ከማንኛውም ነጻነት የበለጠ አስፈላጊነት እንዳለውና ለሌሎቹ ነጻነቶች ሁሉ መሠረት እንደሆነ ያምናሉ። በተጨማሪም አንደኛው ማሻሻያ ምክር ቤት የመንግሥት ሃይማኖት የሚያቋቁም ወይም የሃይማኖት ነጻነትን የሚገድብ ሕግ እንዳያወጣ ይከለክላል።” (ዘ ዎርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፔዲያ) የይሖዋ ምሥክሮችን ጭምር በሚመለከተው በከሳሽ ካንትዌልና በተከሳሽ ኮኔቲከት 310 ዩ ኤስ 296 (1940) ጉዳይ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንደኛው ማሻሻያ በዚህ ማሻሻያ የተረጋገጡትን መብቶች ሕገ መንግሥታዊ ባልሆነ መንገድ የሚገድብ ሕግ እንዳያወጡ የሚያግደው “ምክር ቤቱን” (ፌደራል መንግሥቱን) ብቻ ሳይሆን የክልልና የማዘጋጃ ቤት መስተዳድሮችን ጭምር እንደሆነ በይኗል።

[በገጽ 5 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

ክርክሮቹ ከቤት ወደ ቤት የሚደረጉ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን የሚመለከቱ ነበሩ

[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ የሥዕሎቹ ምንጭ]

Photograph by Franz Jantzen, Collection of the Supreme Court of the United States