“ልቤን ነካው”
“ልቤን ነካው”
በ1994 የይሖዋ ምሥክሮች የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት የሚያስከትለውን ሐዘን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል የሚያብራራ አንድ ብሮሹር አሳትመው ነበር። ብሮሹሩ ከታተመበት ጊዜ አንስቶ ለብዙዎች መጽናኛ አስገኝቷል።
በቅርቡ በፔንሲልቫኒያ፣ ዩ ኤስ ኤ የምትኖር አንዲት ሴት ለብሮሹሩ ያላትን አድናቆት እንዲህ በማለት በደብዳቤ ገልጻለች:- “ብሮሹሩ መጀመሪያ ሲደርሰኝ ‘በጣም ጥሩ ጽሑፍ ነው’ ከማለት ሌላ ስለሚሰጠው ጥቅም ብዙም አላሰብኩም ነበር። ከሁለት ሳምንት በፊት ሴት ልጄ ስትሞት ግን ብሮሹሩ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ተገነዘብኩ። በሐዘን ተውጬ ሳለሁ እርዳታ ለማግኘት ፈለግሁና ብሮሹሩን ማንበብ ጀመርኩ። በዚህ ጊዜ ግን ብሮሹሩ ልቤን ነካው። ለሐዘኔ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች በሙሉ ያካተተ ከመሆኑም በላይ መጽናኛ አግኝቼበታለሁ።”
የምትወዱት ሰው ሲሞት የተሰኘው ብሮሹር እንደሚከተሉት ላሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል:- ከሐዘኔ ልጽናና የምችለው እንዴት ነው? ሌሎች እንዴት መርዳት ይችላሉ? ሙታን ምን ተስፋ አላቸው?
ምናልባት እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሌላ ሰው ይህን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር በማንበብ መጽናኛ ማግኘት ትችሉ ይሆናል። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።
□ የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።