በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘ንቁ! ሕይወቴን አተረፈልኝ!’

‘ንቁ! ሕይወቴን አተረፈልኝ!’

‘ንቁ! ሕይወቴን አተረፈልኝ!’

ንቁ ! መጽሔት አዘጋጆች ከኢጣሊያ አንድ የአድናቆት ደብዳቤ ይደርሳቸዋል። ደብዳቤው በከፊል እንዲህ ይላል:-

“የንቁ ! መጽሔትን ለ40 ዓመታት አንብቤያለሁ፤ በሚዳስሳቸው የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችና በሚሰጣቸው ተግባራዊ ሐሳቦች በጣም አደንቀዋለሁ። በቅርቡ በሥራ ቦታዬ እያለሁ በሆዴና ደረቴ አካባቢ ኃይለኛ ሕመም ተሰማኝ። ወደ ቤት ለመሄድ እያሰብኩ ሳለ እንደገና ተመሳሳይ ሕመም ተሰማኝ፤ በዚህ ወቅት አንድ ነገር በአእምሮዬ ብልጭ አለ። በንቁ ! መጽሔት ላይ የወጣ ስለ ልብ ሕመም ምልክቶች የሚናገር አንድ ርዕስ ትዝ አለኝ። * ስለዚህ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ወሰንኩ። በሆስፒታል ውስጥ ተራ እየጠበቅሁ ሳለ ራሴን ሳትኩና ተዝለፈለፍኩ። ይህንን ያወቅሁት ከፍተኛ እንክብካቤ ወደሚደረግበት ክፍል ከገባሁ በኋላ ነው።

“ዶክተሮች ከፍተኛ ርብርብ ስላደረጉልኝ ዛሬ በሕይወት ልገኝ ችያለሁ። ይሁን እንጂ የእናንተ መጽሔትም ወደ ሆስፒታል ለመሄድ እንድወስን ያደረገኝን መረጃ ስላቀረበልኝ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ንቁ ! ሕይወቴን አትርፎልኛል!”

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.3 የታኅሣሥ 8, 1996 (እንግሊዝኛ) እትማችንን ገጽ 6 ተመልከት።