“ሁሉም ሰው ሊያነብበው የሚገባ መጽሐፍ ነው”
“ሁሉም ሰው ሊያነብበው የሚገባ መጽሐፍ ነው”
ታዋቂው ዴንማርካዊ ደራሲ ኤሪክ ሆስት እንዲህ ሲል የተናገረው ስለ የትኛው መጽሐፍ ነው?
የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ
እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ዴንማርክ ውስጥ እንደ ስህተት የሚቆጠሩ ብዙ ነገሮች አሉ። አሁን ግን ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ልፈጽም ነው። በዴንማርክ ስለ ይሖዋ ምሥክሮች መልካም ነገር መናገር ኮም-ኢል-ፎ [ጥሩ ምግባር] ተደርጎ አይታይም። እኔ ግን ስለ እነርሱ መልካም ጎን መናገር እፈልጋለሁ።
“ለበርካታ ዓመታት ሥርዓታማ አለባበስ ያላቸው አንድ ባልና ሚስት በየወሩ ወደ ቤቴ እየመጡ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ሲሰጡኝ ቆይተዋል። ገና ከመጀመሪያው በምንም ዓይነት ሃይማኖቴን እንደማልቀይር ነግሬያቸው ነበር። ይሁን እንጂ ስለ እምነታቸው ከሚጠቅሷቸው ሐሳቦች በስተቀር መጽሔቶቻቸው ትምህርት ሰጪና አስደሳች ናቸው። በእነዚህ መጽሔቶች ውስጥ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚዳስሱ ግሩም ትምህርቶችን ያነበብኩ ሲሆን [21 ሚልዮን] በሚያህሉ ቅጂዎች የሚሰራጩ መሆኑም አድናቆት ሊቸራቸው እንደሚገባ ያሳያል።
“ባለፈው ጊዜ ባልና ሚስቱ ይህን መጽሐፍ [የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ ] ያለ ምንም ክፍያ ሰጡኝ። . . . መጽሐፉን ከዳር እስከ ዳር አነበብኩት። እንዲሁም በውስጡ በዋቢነት ከተጠቀሱት በርካታ ጽሑፎች መካከል አብዛኞቹን አመሣከርኩ።
“እስከዛሬ ካነበብኳቸው ስለ ሃይማኖት ታሪክ የሚናገሩ መጽሐፎች ሁሉ የተሻለ፣ እውነታውን ቁልጭ አድርጎ የሚገልጽና ለየትኛውም ወገን የማያደላ መጽሐፍ ነው።
“ሁሉም ሰው ሊያነብበው የሚገባ መጽሐፍ ነው ብዬ በሙሉ ልብ መናገር እችላለሁ። እርግጥ ስለ ይሖዋ ምሥክሮች እምነት የሚናገር ሐሳብም ይዟል። ሆኖም ይህ የሃይማኖትን ታሪክ ግሩም በሆነ መንገድ በሚያቀርበው በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በጥቂቱ ተጠቅሶ የታለፈ ጉዳይ ነው።”
ይህን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው ይላኩ።
□ የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።
[የሥዕሎቹ ምንጮች]
ከላይ በስተ ግራ፣ አይሁዳዊ:- Garo Nalbandian; ከላይ መሃል ያለው፣ የቡድሃ መነኩሴ:- G. Deichmann, Transglobe Agency, Hamburg