በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለኅብረተሰቡ ጠቃሚ ናቸው

ለኅብረተሰቡ ጠቃሚ ናቸው

ለኅብረተሰቡ ጠቃሚ ናቸው

ስፔይን የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው

ለበርካታ መቶ ዓመታት በስፔይን ከተሞች የአምልኮ ሕንፃ የሚሠራበት ቦታ በነጻ ሲሰጥ ቆይቷል። የከተሞቹ መስተዳድሮች ሃይማኖት ለኅብረተሰቡ ጠቃሚ ነው ብለው ያምኑ ነበር። የካቶሊክ እምነት የመንግሥት ሃይማኖት ስለነበረ በማዘጋጃ ቤቱ ንብረቶች የመጠቀም ሙሉ መብት የተሰጠው ለካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነበር ማለት ይቻላል። አሁን ግን ጊዜው ተለውጧል።

በ1980 “የትኛውም ሃይማኖት የመንግሥት ሃይማኖት አይሆንም” የሚል ሃይማኖታዊ ነጻነትን የሚያስከብር ሕግ ወጣ። ይህ ሕግ አንዳንድ የማዘጋጃ ቤት ባለ ሥልጣናት የይሖዋ ምሥክሮች ለሚያከናውኑት ሥራ ሕጋዊ እውቅና እንዲሰጡ ገፋፍቷቸዋል። ይህንንም በተግባር ለማሳየት ለመንግሥት አዳራሽ መሥሪያ የሚሆኑ ቦታዎችን በነጻ ሰጥተዋል።

በርካታ የከተማ መስተዳድሮች የይሖዋ ምሥክሮች “የስብከት ሥራ ትምህርት ሰጪ በመሆኑ” እንዲሁም “ለማኅበረሰቡ ጠቃሚ አስተዋጽኦ ስለሚያበረክቱ” የአዳራሽ መሥሪያ ቦታ ማግኘታቸው ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል። ሌሎች የማዘጋጃ ቤት ባለ ሥልጣናትም “የይሖዋ ምሥክሮች በከተማው ውስጥ መኖራቸው በራሱ በጣም ጠቃሚ መሆኑን” እና “የስብከት ሥራቸው ትርፍ ለማግኘት ተብሎ የሚደረግ አለመሆኑን” ጠቅሰዋል።

አብዛኞቹ አዳራሾች የተገነቡት ፈቃደኛ ሠራተኞችን ያቀፉት የግንባታ ቡድኖች በሚጠቀሙበት ልዩ የግንባታ ዘዴ አማካኝነት ሲሆን ሥራው የሚወስደው ጊዜ ከ48 ሰዓት አይበልጥም። በደቡብ ምዕራብ ስፔይን የምትገኝ ላ ሊኔያ የተባለች ከተማ ከንቲባ እንዲህ የሚል አስተያየት ሰጥተዋል:- “ፈቃደኛ ሠራተኞቹ ምንም ሳይቆጥቡ ራሳቸውን ማቅረባቸው በጣም አስገርሞኛል፤ እኛም ድጋፍ ልናደርግላቸው እንደሚገባን ይሰማኛል። በጊዜያችን ባለው የተከፋፈለ ዓለም ውስጥ እንዲህ ያለው የትብብር መንፈስ በጣም ያስፈልገናል።” አዲስ የተገነባውን የመንግሥት አዳራሽ “የትብብር መንፈስ ተምሳሌት” በማለት ጠርተውታል።

አዳራሾቹ በተሠሩባቸው ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎችም ይህን የትብብር መንፈስ ተመልክተዋል። በሰሜናዊ ስፔይን በምትገኘው ቪቶሪያ ከተማ ሁለት አዳራሾች ያሉት ሕንፃ በተገነባበት ወቅት በአካባቢው የምትኖር ማሪያን የተባለች ሴት “ሁሉም ሰው እንዲህ ያለ ፍቅር ቢኖረው ኖሮ በጊዜያችን ያሉት ችግሮች ባልኖሩ ነበር” ብላለች። ግንባታውን የተመለከተ አንድ በአካባቢው የሚኖር የሕንፃ ተቋራጭ “ደስታችሁን ለመጋራት ስል የይሖዋ ምሥክር መሆን እፈልጋለሁ” ብሏል።

በሰሜናዊ ምሥራቅ ስፔይን በምትገኘው በዛራጎዛ ከተማ የማዘጋጃ ቤቱ ባለ ሥልጣናት ለይሖዋ ምሥክሮች 600 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቦታ በነጻ ሰጥተዋል። አንድ የአካባቢው ጋዜጣ የግንባታ ቦታውን “በመቶዎች የሚቆጠሩ ትናንሽ ጉንዳኖች በኅብረት ከሚሠሩበት የጉንዳን ኩይሳ” ጋር አወዳድሮታል። የአካባቢው ሰዎች ለግንባታው ሠራተኞች ሞቅ ያለ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በተለይ አንዲት ሴት “በቄሶች ምክንያት ያጣሁትን በአምላክ ላይ ያለኝን እምነት እናንተ መልሳችሁልኛል” በማለት ተናግራለች።

የይሖዋ ምሥክሮች የአምልኮ ቦታዎቻቸውን በሚገነቡበት ወቅት የአካባቢው ሰዎችም ሆኑ ባለ ሥልጣናት ላደረጉላቸው ትብብር አመስጋኞች ናቸው። አዳራሾቻቸውን ኅብረተሰቡን እጅግ ለሚጠቅም ሥራ ይኸውም የአምላክን ቃል ለመስበክና ለማስተማር ሊጠቀሙበት ቁርጥ ውሳኔ አድርገዋል።

[በገጽ 20 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ላ ሊኔያ፣ ካዲዝ፣ ስፔይን