ከምንወደው ሰው የተላከ ደብዳቤ
ከምንወደው ሰው የተላከ ደብዳቤ
ወደ ይሖዋ ቅረቡ የተባለውን መጽሐፍ ያነበበች አንዲት ሴት መጽሐፉን ከምንወደው ሰው ከተላከ ደብዳቤ ጋር በማመሳሰል እንዲህ ብላለች:- “እያንዳንዱ ምዕራፍ ልብን በጥልቅ የሚነካ ሲሆን ይሖዋን ይበልጥ እንድትወዱት ያደርጋል። መጽሐፉን አንድ ጊዜ አንብቤ ጨርሻለሁ። ከምትወዱት ሰው የተላከላችሁን ደብዳቤ ደግማችሁ እንደምታነቡት ሁሉ እኔም መጽሐፉን እንደገና እስከምጀምረው ቸኩያለሁ።” ሌሎች ደግሞ ምን እንዳሉ ተመልከት።
በካንሳስ የምትኖር መጽሐፉን ያነበበች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች:- “ወደ ሰማዩ አባቴ ይበልጥ እንደቀረብኩ ይሰማኛል። ልቤ ለይሖዋ ባለኝ ፍቅር ተሞልቷል። . . . በየዕለቱ ጠዋት ተጨማሪ የመጽሐፉን ክፍሎች ለማንበብ እናፍቃለሁ። መጽሐፉን ወደፊትም ደግሜ ደጋግሜ አነብበዋለሁ።”
በዩ ኤስ ኤ፣ ሜን ግዛት የምትኖር አንዲት ሴት ደግሞ እንዲህ ስትል ጽፋለች:- “ስለ ይሖዋ ህልውና ያለኝን ግንዛቤ በእጅጉ አሳድጎልኛል። በተለይ በገጽ 74 ላይ ያለው ‘ሙታን አምላክ በትንሣኤ ከሚያስባቸው ሰዎች መካከል ከመሆን የተሻለ አስተማማኝ ዋስትና ሊኖራቸው አይችልም’ የሚለው ዓረፍተ ነገር በእጅጉ አጽናንቶኛል።” በአላስካ የምትኖር አንዲት ሴት ተመሳሳይ ሐሳብ አላት:- “መጽሐፉ ልቤን ስለነካው እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም።” አክላም “ወደፊትም ደጋግሜ አነብበዋለሁ፤ እንዲሁም አስፈላጊ ሲሆን አንዳንዶቹን ሐሳቦች ተመልሼ እመለከታቸዋለሁ።”
እርስዎም ይህን መጽሐፍ ቢያነቡ እንዲህ እንደሚሰማዎ እንተማመናለን። መጽሐፉ ከመጀመሪያዎቹ ሦስት የመግቢያ ምዕራፎች በኋላ “ኃይሉ እጅግ ታላቅ ነው፣” “ፍትሕን ይወዳል፣” “ልቡ ጠቢብ ነው” እንዲሁም “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” በሚሉ አራት ክፍሎች ተከፋፍሏል። የሚደመድመውም “ወደ አምላክ ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል” በሚል ምዕራፍ ነው።
እርስዎም ይህን ባለ 320 ገጽ መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ ወደ ይሖዋ ቅረቡ የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።