በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ያቀረበችው ሪፖርት ከፍተኛ አድናቆት አትርፏል

ያቀረበችው ሪፖርት ከፍተኛ አድናቆት አትርፏል

ያቀረበችው ሪፖርት ከፍተኛ አድናቆት አትርፏል

በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር ጂኒ የተባለች አንዲት የይሖዋ ምሥክር የመጨረሻ ዓመት ተማሪ ሳለች ስለ ሃይማኖቷ የምትናገርበት ግሩም አጋጣሚ አግኝታ ነበር። እንዲህ ትላለች:- “አስተማሪያችን የመመረቂያ ጽሑፍ እንድናዘጋጅ አዘዘችን። እኔም የይሖዋ ምሥክሮች በናዚ ማጎሪያ ካምፖች ውስጥ ስለደረሰባቸው መከራ መጻፍ እንደምፈልግ ነገርኳት።”

አስተማሪዋ በዚህ ርዕስ እንድትጽፍ ፈቀደችላት። “የመመረቂያ ጽሑፌን ለአስተማሪዋ የምሰጥበትና ለክፍሉ ተማሪዎች በንግግር የማቀርብበት ቀን ሲቃረብ ፍርሃት ተሰምቶኝ ነበር። ተማሪዎቹ ምን ይሉኛል፤ ያሾፉብኝ ይሆን? ብዬ አስቤ ነበር” በማለት የተሰማትን ተናግራለች።

ጂኒ ንግግሯን የጀመረችው “በናዚ ማጎሪያ ካምፖች ውስጥ የዳዊት ኮከብ የተለጠፈበት ልብስ ይለብሱ የነበሩት እነማን እንደሆኑ ታውቃላችሁ?” በሚል ጥያቄ ነበር። ተማሪዎቹ በአንድነት “አይሁዶች” ሲሉ መለሱ። ከዚያም ባለ ሦስት ማእዘን ወይን ጠጅ ጨርቅ የተሰፋበት ልብስ የለበሱት እነማን እንደሆኑ ጠየቀቻቸው። ማንም መልስ አልሰጠም። ጂኒ “የይሖዋ ምሥክሮች እንደሆኑ ነገርኳቸው” በማለት ተናግራለች።

አስተማሪዋና የክፍሉ ተማሪዎች በጂኒ ንግግር በጣም ተደነቁ። ጂኒ እንዲህ ትላለች:- “የይሖዋ ምሥክሮች እምነታቸውን መካዳቸውን በሚገልጽ ቅጽ ላይ ቢፈርሙ ወዲያውኑ ይለቀቁ እንደነበር ሲያውቁ በጣም ተገረሙ። አንዳንዶቹ የክፍሌ ተማሪዎች ደግሞ ከዚህ በፊት በይሖዋ ምሥክሮች ላይ ያፌዙ እንደነበርና ከአሁን በኋላ ግን የይሖዋ ምሥክሮች ቤታቸው ሲመጡ ጆሮ ሰጥተው እንደሚያዳምጧቸው ነግረውኛል።”

ጂኒ በመመረቂያ ጽሑፏና ባቀረበችው ንግግር አራት “ኤ” አግኝታለች። “ጥሩ ውጤት ብቻ ሳይሆን ስለ እምነቴ ለሌሎች ለመናገር የሚያስችል ግሩም አጋጣሚም አግኝቻለሁ” ብላለች።

[በገጽ 29 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

አብዛኞቹ የይሖዋ ምሥክሮች እምነታቸውን መካዳቸውን ለመግለጽ ይህን ቅጽ ከፈረሙ በነጻ መለቀቅ ይችሉ ነበር

[ምንጭ]

Courtesy of United States Holocaust Memorial Museum