በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘መልካም አድርጉ’

‘መልካም አድርጉ’

‘መልካም አድርጉ’

“የምታደርጉት ጥረትና ትጋት የተሞላበት እንቅስቃሴ የከተማችን ውበትና ለጎብኚዎች ያለው መስህብነት ከሚያሳስባቸው ሰዎች እይታ የተሰወረ እንዳልሆነ እንድታውቁ እወዳለሁ። የቅርንጫፍ ቢሯችሁ ሕንጻ ለአካባቢያችሁና ለከተማው ውበት እንደምትጨነቁ ምሥክር ነው።”

እነዚህን የምስጋና ቃላት የተናገሩት በካናዳ የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ የሚገኝበት የሃልተን ሂልስ ከተማ ከንቲባ ናቸው። ከንቲባው ይህን ካሉ በኋላ “የሃልተን ሂልስ ከተማ ነዋሪዎችን ሕይወት ለማሻሻል የምታደርጉትን ጥረት እናደንቃለን” የሚል ጽሑፍ የተቀረጸበት ጽላት ለቅርንጫፍ ቢሮው ሰጥተዋል።

ከመንግሥት ባለ ሥልጣናት የሚሰነዘረው እንዲህ ያለው የአድናቆት መግለጫ “መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል” የሚሉት የሮሜ 13:3 ቃላት ያላቸውን እውነተኝነት የሚያረጋግጥ ነው። ይሁን እንጂ ለዚህ ሊወደስና ሊከበር የሚገባው የአጽናፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ጌታ የሆነው ይሖዋ ነው።