የብልግና ሥዕሎች የሚያስከትሉት ጉዳት
የብልግና ሥዕሎች የሚያስከትሉት ጉዳት
ዛሬ ማንኛውንም የወሲብ መረጃ ከቴሌቪዥን፣ ከፊልሞች፣ ከሙዚቃ ፊልሞችና ከኢንተርኔት በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። ታዲያ በእነዚህ የብልግና ሥዕሎች መጥለቅለቃችን ብዙዎች ሊያሳምኑን እንደሚሞክሩት የሚያስከትሉት ምንም ዓይነት ጉዳት የለውም? *
የብልግና ሥዕሎች በትላልቅ ሰዎች ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉት ጉዳት
የብልግና ሥዕሎች ደጋፊዎች ያሉትን ቢሉ የብልግና ሥዕሎች ሰዎች ለወሲብ ባላቸው አመለካከት ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። በቤተሰብ ምርምርና ትምህርት ብሔራዊ ተቋም የሚሠሩ ተመራማሪዎች “ለብልግና ሥዕሎች መጋለጥ ፆታን በተመለከተ በተመልካቹ ላይ ጤናማ ያልሆነ ዝንባሌ እንዲያድር ያደርጋል” ብለዋል። ይህ ሪፖርት እንደሚለው “ሴቶች ተገድዶ መደፈር ያስደስታቸዋል፣ ሴቶችን አስገድደው የሚደፍሩ ምንም ጉድለት የሌላቸው ጤናማ ሰዎች ናቸው የሚለው አጉል እምነት የብልግና ሥዕሎችን አዘውትረው በሚመለከቱ ወንዶች ላይ በአብዛኛው ተስፋፍቶ ይገኛል።”
አንዳንድ ተመራማሪዎች እንደሚሉት የብልግና ሥዕሎችን በተደጋጋሚ መመልከት በጋብቻ ውስጥ በሚፈጸም ጤናማ የሆነ ሩካቤ ሥጋ የመደሰት ችሎታን ያሳጣል። የወሲብ ሱስ ሐኪም የሆኑት ዶክተር ቪክተር ክላይን የብልግና ፊልም ተመልካቾች ቁጥር እየጨመረ መሄዱን አስተውለዋል። ቶሎ ካልተተወ እንደ አጋጣሚ የተጀመረው የብልግና ሥዕሎችን የማየት ልማድ ሥር ሊሰድድና ይበልጥ አስነዋሪ የሆኑ የብልግና ሥዕሎችን ወደ መመልከት ሊያመራ ይችላል። ይህ ደግሞ ከተፈጥሮ ውጭ የሆኑ ድርጊቶችን ወደመፈጸም ሊያመራ ይችላል። የሥነ ባሕርይ አጥኚዎች በዚህ ይስማማሉ። ዶክተር ክላይን “ማንኛውም ዓይነት ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ የወሲብ ባሕርይ በዚህ መንገድ
ሊመጣ የሚችል ሲሆን . . . ምንም ዓይነት የፀፀት ስሜት ሊያስወግደው አይችልም” ብለዋል። ውሎ አድሮ ተመልካቹ አእምሮው ውስጥ የተቀረጸውን የብልግና ቅዠት በተግባር ለማዋል ሊነሳሳና ይህም ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስበት ይችላል።የችግሩ አጀማመር በጣም አዝጋሚና ቶሎ የማይታወቅ ሊሆን እንደሚችል ክላይን ይናገራሉ። እንዲህ ይላሉ:- “እንደ ካንሰር ውስጥ ውስጡን ማደግና መሰራጨት ይጀምራል። ይህን ሂደት አብዛኛውን ጊዜ ማስቆም የማይቻል ከመሆኑም በላይ በሽታውን ማከምም ሆነ ማዳን አይቻልም። ወንድ ሱሰኞች ችግር እንዳለባቸው ለመቀበልና ችግሩን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ፈቃደኛ አለመሆናቸው የተለመደና የሚጠበቅ ነው። በዚህም ምክንያት ሁልጊዜ ማለት ይቻላል በባልና ሚስቶች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ሲያደርግ እስከ መፋታትም ሊያደርስ ይችላል። ሌሎች ግንኙነቶችም የሚቋረጡበት ጊዜ ይኖራል።”
በወጣቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት
ስታቲስቲካዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ዋነኞቹ የብልግና ሥዕል ደንበኞች በ12 እና በ17 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወንዶች ልጆች ናቸው። እንዲያውም አብዛኞቹ ልጆች ስለ ወሲብ የሚማሩት ከብልግና ሥዕሎች ነው። ይህ ደግሞ በጣም አሳሳቢ የሆነ ችግር ያስከትላል። አንድ ዘገባ እንደሚለው “በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ልጆች እርግዝናና እንደ ኤድስ ያሉት በፆታ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች በብልግና ሥዕሎች ውስጥ ፈጽሞ አይታዩም። ይህም ሥዕሎቹ የሚያደርሱት ምንም ዓይነት ጉዳት የለም የሚል የተሳሳተ እምነት ያሳድራል።”
አንዳንድ ተመራማሪዎች ደግሞ የብልግና ሥዕሎችን መመልከት የአንድን ሕፃን ተፈጥሯዊ የአእምሮ እድገት ሊገታ እንደሚችል ተናግረዋል። የሕክምና ትምህርት ተቋም ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶክተር ጁዲት ራይስማን እንዲህ በማለት ደምድመዋል:- “አንጎል ለብልግና ሥዕሎችና ድምፆች የሚሰጠው ቅጽበታዊ ምላሽ በነርቭ ጤንነት ላይ ምን ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል በተደረገው ጥናት የብልግና ሥዕሎችን መመልከት አእምሮ አስቦና አመዛዝኖ መረጃ የመውሰድ ችሎታውን እንደሚያሳጣው ለማወቅ ተችሏል። ይህም ልጆች ስለ ገሀዱ ዓለም ያላቸውን ግንዛቤ ስለሚያበላሽባቸውና በዚህም ምክንያት አካላዊና አእምሮአዊ ጤንነታቸውን፣ የወደፊት ደህንነታቸውንና ደስታ የማግኘት አጋጣሚያቸውን ስለሚጎዳባቸው ገና ባልጠነከረውና በቀላሉ ሊቀረጽ በሚችለው አንጎላቸው ላይ ጉዳት ያደርሳል።”
በሰብዓዊ ግንኙነቶች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት
የብልግና ሥዕሎች የሰዎችን ዝንባሌና ባሕርይ ይቀርጻሉ። በዋነኝነት በቅዠት ላይ የተመሠረቱ በመሆናቸውና ከእውነታው ውጭ የሆነ ስሜት ስለሚፈጥሩ የሚያስተላልፉት መልእክት አታላይ ነው። (“የምትቀበለው የትኛውን መልእክት ነው?” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።) “የብልግና ሥዕሎችን የሚመለከቱ ግለሰቦች ከወሲብ የሚጠብቁት ነገር ከእውነታ ውጭ ስለሆነ ከተቃራኒ ጾታ ጋር ያላቸው ግንኙነት ይበላሻል” በማለት አንድ ዘገባ ይገልጻል።
የብልግና ሥዕሎች ለተሳካ ትዳር በጣም አስፈላጊ የሆነውን መተማመንና ግልጽነት ያጠፋሉ። የብልግና ሥዕሎች አብዛኛውን ጊዜ የሚታዩት በድብቅ ስለሆነ ወደማታለልና መዋሸት ይመራሉ። የትዳር ጓደኞች ክህደት እንደተፈጸመባቸው ሆኖ ይሰማቸዋል። የትዳር ጓደኞቻቸው ማራኪ ሆነው ያላገኟቸው ለምን እንደሆነ ግራ ይገባቸዋል።
መንፈሳዊ ጉዳት
የብልግና ሥዕሎችን መመልከት ከባድ መንፈሳዊ ጉዳት ያደርሳል። ከአምላክ ጋር ለመዛመድ ለሚፈልግ ግለሰብ ከባድ እንቅፋት ሊሆንበት ይችላል። * መጽሐፍ ቅዱስ ፍትወትን ከመጎምጀትና ከጣዖት አምልኮ ጋር ያዛምደዋል። (ቆላስይስ 3:5) አንድን ነገር የሚጎመጅ ሰው በሕይወቱ ውስጥ ዋነኛ ቦታ የሚሰጠው ለሚጎመጅለት ነገር ስለሚሆን ሌላው ነገር ሁሉ ሁለተኛ ደረጃ ይይዛል። የብልግና ሥዕሎችን የማየት ሱስ የተጠናወታቸው ሰዎች የፆታ ፍላጎታቸውን ከአምላክ በላይ ያደርጋሉ ማለት ነው። በዚህ መንገድ እንደ ጣዖት ያመልኩታል። የይሖዋ ትእዛዝ ደግሞ “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ” ይላል።—ዘጸአት 20:3
የብልግና ሥዕሎች በፍቅር ላይ የተመሠረቱ ዝምድናዎችን ያበላሻሉ። ባለ ትዳር የነበረው ሐዋርያው ጴጥሮስ ክርስቲያን ባሎች ሚስቶቻቸውን ማክበር እንደሚገባቸው መክሯል። ሚስቱን የማያከብር ባል ለአምላክ የሚያቀርበው ጸሎት ይታገድበታል። (1 ጴጥሮስ 3:7) የሌሎች ሴቶችን አስነዋሪ ምስል ተደብቆ የሚመለከት ሰው ለገዛ ሚስቱ አክብሮት አለኝ ብሎ ሊናገር ይችላል? እርሷስ ይህን ብታውቅ ምን ይሰማታል? “ሥራን ሁሉ . . . ወደ ፍርድ” የሚያመጣውና ‘መንፈስን የሚመዝነው’ አምላክስ ምን ይሰማዋል? (መክብብ 12:14፤ ምሳሌ 16:2) የብልግና ሥዕሎችን የሚመለከት ሰው ጸሎቱ በአምላክ ዘንድ ተሰሚነት ያገኛል ብሎ ሊጠብቅ ይችላል?
የመጣው ይምጣ የሚለው አመለካከት የብልግና ሥዕል 1 ተሰሎንቄ 4:3-7
ሱሰኞች ዋነኛ ባሕርይ ነው። ስለዚህ የብልግና ሥዕሎችን የሚመለከት ሰው ፍቅር ይጎድለዋል። አንድ ክርስቲያን ንጽሕናውን ለመጠበቅና በአምላክ ፊት ንጹሕ ሥነ ምግባር ይዞ ለመገኘት የሚያደርገውን ትግል ያዳክምበታል። ሐዋርያው ጳውሎስ “ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፣ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፣ . . . ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ ወንድሙንም አያታልል” በማለት ጽፏል።—የብልግና ሥዕሎች በተለይ በሴቶችና በሕፃናት ላይ በደል ይፈጽማሉ፤ ያዋርዷቸዋል፣ ክብራቸውንና መብታቸውንም ይገፍፏቸዋል። የብልግና ሥዕሎችን የሚመለከት ሰው በዚህ በደል ተካፋይና ተባባሪ ይሆናል። ስቲቨን ሂል እና ኒና ሲልቨር የተባሉት ተመራማሪዎች “አንድ ሰው ምንም ያህል ጨዋ ነኝ ብሎ ቢያስብ . . . የብልግና ሥዕሎችን የሚመለከትና የሚደግፍ ከሆነ ቢያንስ እወደዋለሁ፣ አስብለታለሁ ለሚለው ግለሰብ ደህንነት ደንታ ቢስ ከዚያም አልፎ ጠላት ወይም ተጠራጣሪ መሆኑ አይቀርም” ብለዋል።
የብልግና ሥዕሎችን ከመመልከት ሱስ መላቀቅ
የብልግና ሥዕሎችን የማየት ሱስ ካለብህና ከዚህ ሱስ ለመላቀቅ በመጣር ላይ ከሆንክስ? ከዚህ ሱስ ለመላቀቅ ምን ልታደርግ ትችላለህ? መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ይሰጣል። ከጥንት ክርስቲያኖች መካከል አንዳንዶቹ ክርስቶስን ከማወቃቸው በፊት አመንዝሮች፣ ሴሰኞችና ስግብግቦች ነበሩ። ጳውሎስ “ታጥባችኋል” ብሏል። ይሄ የሆነው እንዴት ነው? “በአምላካችንም መንፈስ . . . ተቀድሳችኋል” በማለት መልሱን ይሰጣል።—1 ቆሮንቶስ 6:9-11
የአምላክ ቅዱስ መንፈስ ያለውን ኃይል አቅልለህ አትመልከት። መጽሐፍ ቅዱስ “ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ 1 ቆሮንቶስ 10:13) ችግርህን እየጠቀስክ አለመታከት ለአምላክ የምታቀርበው ልባዊ ጸሎት ውጤት ማስገኘቱ አይቀርም። የአምላክ ቃል “ትካዜህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል፣ እርሱም ይደግፍሃል፤ ለጻድቁም ለዘላለም ሁከትን አይሰጠውም” ይላል።—መዝሙር 55:22
ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው” ይላል። በእርግጥም አምላክ መውጫውን ያዘጋጃል። (እርግጥ ከጸሎትህ ጋር የሚስማማ እርምጃ መውሰድ ይኖርብሃል። ከብልግና ሥዕሎች ለመራቅ ልባዊና ቁርጥ ያለ ውሳኔ ማድረግ ያስፈልግሃል። የታመነ ወዳጅ ወይም የቤተሰብ አባል ባደረግኸው ውሳኔ እንድትጸና ማበረታቻና ድጋፍ በመስጠት በጣም ጠቃሚ የሆነ እርዳታ ሊሰጥህ ይችላል። (“እርዳታ ማግኘት” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።) ይህ የምታደርገው ጥረት አምላክን እንደሚያስደስተው ማስታወስህ በዚህ አካሄድህ እንድትጸና ይረዳሃል። (ምሳሌ 27:11) በተጨማሪም የብልግና ሥዕሎችን ማየት አምላክን እንደሚያስከፋው ማወቅህ ከዚህ ልማድ እንድትላቀቅ ተጨማሪ ግፊት ይሰጥሃል። (ዘፍጥረት 6:5, 6) ቀላል ትግል ባይሆንም በድል ልትወጣው ትችላለህ። የብልግና ሥዕሎችን ከመመልከት ልማድ መላቀቅ ይቻላል!
የብልግና ሥዕሎችን መመልከት አደገኛ ነው። ጉዳትና ጥፋት ያስከትላል። ሥዕሎቹን የሚያዘጋጁትንም ሆነ የሚመለከቱትን ሰዎች ያበላሻል። ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን የሚያዋርድ ልማድ ነው። በልጆች ላይ ትልቅ አደጋ ያስከትላል። በእርግጥም ሊወገድ የሚገባው ልማድ ነው።
[የግርጌ ማስታወሻዎች]
^ አን.2 በኢንተርኔት የሚተላለፉ የብልግና ሥዕሎች ስለሚያስከትሉት ጉዳት የተብራራ መረጃ ለማግኘት በሰኔ 8, 2000 የእንግሊዝኛ ንቁ! መጽሔት ከገጽ 3-10 ላይ “በኢንተርኔት የሚተላለፉ የብልግና ሥዕሎች—ምን ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።
^ አን.14 መጽሐፍ ቅዱስ ለብልግና ሥዕሎች ስላለው አመለካከት የነሐሴ 2002 ንቁ! እትም ገጽ 27-29ን ተመልከት።
[በገጽ 10 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]
እርዳታ ማግኘት
የብልግና ሥዕሎችን ከመመልከት ልማድ መላቀቅ እንደ ቀላል ነገር መታየት አይኖርበትም። መታገልን የሚጠይቅ ሊሆን ይችላል። በመቶ ለሚቆጠሩ ሱሰኞች ክትትል ያደረጉት ዶክተር ቪክተር ክላይን “ቃል መግባት ብቻውን በቂ አይሆንም። በጥሩ ግፊት መነሳሳትም ምንም ትርጉም የለውም። [አንድ የብልግና ሥዕሎች ሱሰኛ] በራሱ ኃይል ይህን ማድረግ አይችልም” ብለዋል። የተሳካ ውጤት ለማግኘት ቁልፍ የሆነው ነገር ሰውየው ያገባ ከሆነ የትዳር ጓደኛው በዚህ ጥረቱ ተካፋይ እንድትሆን ማድረግ ነው። “ሁለቱም የሚረዳዱ ከሆነ ፈጣን ለውጥ ማግኘት ይቻላል” ብለዋል። “የቆሰሉት ሁለቱም ስለሆኑ ሁለቱም እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።”
ግለሰቡ ያላገባ ከሆነ አንድ የሚያምነው ወዳጅ ወይም የቤተሰብ አባል እንደምሰሶ ሊያጠነክረው ይችላል። ለመላቀቅ በምታደርገው ጥረት ማንም ይርዳህ ማን፣ ክላይን ሊለወጥ የማይችል አንድ ሕግ አላቸው። ስለ ችግርህና ችግርህ ስለማገርሸቱ በግልጽ ተነጋገር። “መደበቅ ‘ይገድልሃል’” ይላሉ። መደበቅ “እፍረትና የበደለኝነት ስሜት ይፈጥራል።”
[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ ግራፍ]
የምትቀበለው የትኛውን መልእክት ነው?
የብልግና ሥዕሎች የሚያስተላልፉት መልእክት
▪ ከማንም ጋር፣ በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛውም ሁኔታና መንገድ የፆታ ግንኙነት መፈጸም ጥሩ ነው፣ ምንም ጉዳት አያስከትልም።
የመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት
▪ “መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።”—ዕብራውያን 13:4
“ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል።”—1 ቆሮንቶስ 6:18፤ በተጨማሪም ሮሜ 1:26, 27ን ተመልከት።
የብልግና ሥዕሎች የሚያስተላልፉት መልእክት
▪ ጋብቻ ለወሲብ እርካታ እንቅፋት ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት
▪ “ከጉብዝናህም ሚስት ጋር ደስ ይበልህ። . . . በፍቅርዋም ሁልጊዜ ጥገብ።”—ምሳሌ 5:18, 19፤ በተጨማሪም ዘፍጥረት 1:28፤ 2:24፤ 1 ቆሮንቶስ 7:3ን ተመልከት።
የብልግና ሥዕሎች የሚያስተላልፉት መልእክት
▪ የሴቶች ዓላማ አንድ ብቻ ነው። እርሱም የወንዶችን የወሲብ ስሜት ማርካት ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት
▪ “እግዚአብሔር አምላክም አለ:- ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት።”—ዘፍጥረት 2:18፤ በተጨማሪም ኤፌሶን 5:28ን ተመልከት።
የብልግና ሥዕሎች የሚያስተላልፉት መልእክት
▪ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ለወሲብ ፍላጎታቸው ባሮች ናቸው።
የመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት
▪ “እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ፣ እነዚህም ዝሙትና ርኵሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣዖትንም ማምለክ የሆነ መጐምጀት ነው።”—ቆላስይስ 3:5
“ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ [ይወቅ]።”—1 ተሰሎንቄ 4:4
“ጐበዞችን እንደ ወንድሞች፣ የሸመገሉትን ሴቶች እንደ እናቶች፣ ቈነጃጅቱን እንደ እኅቶች በፍጹም ንጽሕና” ተመልከታቸው።—1 ጢሞቴዎስ 5:1, 2፤ በተጨማሪም 1 ቆሮንቶስ 9:27ን ተመልከት።
[በገጽ 7 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
አንዳንድ ተመራማሪዎች የብልግና ሥዕሎችን መመልከት የአንድን ሕፃን አእምሮ እድገት ሊገታ ይችላል ይላሉ
[በገጽ 8 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
የብልግና ሥዕሎች በትዳር ውስጥ መተማመንና ግልጽነት እንዲጠፋ ሊያደርጉ ይችላሉ
[በገጽ 10 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ልባዊ የሆነ ጸሎት ጥሩ ውጤት ያስገኛል