በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ሴቶች—አክብሮት ሊሰጣቸው ይገባል”

“ሴቶች—አክብሮት ሊሰጣቸው ይገባል”

“ሴቶች—አክብሮት ሊሰጣቸው ይገባል”

በሕንድ፣ የምትኖር የኮሌጅ ተማሪ የሆነች አንዲት የ17 ዓመት ወጣት ትምህርት ቤቷ ባዘጋጀው ንግግር የማቅረብ ውድድር ተካፈለች። ንግግሩን ለማዘጋጀት የተጠቀመችው ከጥር–መጋቢት 1995 የንቁ! እትም ላይ “ሴቶች—አክብሮት ሊሰጣቸው ይገባል” በሚል የሽፋን ርዕስ ሥር የወጡትን ሐሳቦች ነበር።

ለንግግሯ የመረጠችው ርዕስ “ሴቶች—በአሁኑ ጊዜ ይከበራሉን?” የሚል ነበር። ምን ውጤት አገኘች? “በውድድሩ አንደኛ ወጣሁ” በማለት ጽፋለች። አክላም እንዲህ ብላለች:- “ንቁ! መጽሔትን ከልቤ እንደማደንቀው መግለጽ እፈልጋለሁ። መጽሔቱ ብዙ ነገር እንድናውቅ እንዲሁም ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖረን ስለሚረዳን እንደ እኛ ላሉ ወጣቶች በጣም ጠቃሚ ነው። በተጨማሪም ይህ ዓለም የሚያሳድርብንን ተጽዕኖ ለመቋቋም ይረዳናል።”

ይህን የንቁ! እትም ወድደኸዋል? ንቁ! ለወጣቶች ብቻ ሳይሆን ለመላው ቤተሰብ የሚጠቅም እውቀት ይገኝበታል። ይህ መጽሔት ከወቅታዊ ሁኔታዎች በስተ ጀርባ ያለውን ትክክለኛ ትርጉም ያስረዳል። በአማርኛ በወር አንድ ጊዜ ይታተማል። አንድም እትም አያምልጥህ!