በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በተገቢው ጊዜ የተገኘ መጽናኛ

በተገቢው ጊዜ የተገኘ መጽናኛ

በተገቢው ጊዜ የተገኘ መጽናኛ

በዚህ የሚያስጨንቅ ዘመን ብዙዎች በተለይ ደግሞ የሚወዱትን ሰው በሞት ያጡ ሰዎች መጽናኛ ማግኘት አስፈልጓቸዋል። አንዲት ሴት እናቷን በሞት በማጣቷና ብዙም ሳይቆይ በማኅፀኗ የነበረው ፅንስ በመጨንገፉ በእጅጉ አዝና ነበር። በሜክሲኮ ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ በጻፈችው ደብዳቤ ላይ እንዲህ ብላለች:- “ከሐዘኔ ያጽናናኝ ትልቁ ነገር የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር ማግኘቴ ነበር። ጠቃሚ የሆነ ሐሳብ የያዘው ይህ ብሮሹር የደረሰኝ ልክ በሚያስፈልገኝ ወቅት ነው። ለክርስቲያናዊ ፍቅራችሁና እንዲህ ያሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን ለማዘጋጀት ለምታደርጉት ትጋት የታከለበት ጥረት ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።”

ይህቺን ሴት በተለይ ያጽናኗት በብሮሹሩ ውስጥ የተጠቀሱት ጥቅሶች ነበሩ። ለምሳሌ ያህል 1 ቆሮንቶስ 15:26 “የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው” ይላል። ምናልባት እርስዎም ሆኑ እርስዎ የሚያውቁት ሌላ ሰው ይህን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር በማንበብ ማጽናኛ ማግኘት ትችሉ ይሆናል። የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለው ብሮሹር “ከሐዘኔ ልጽናና የምችለው እንዴት ነው?፣” “ሌሎች እንዴት መርዳት ይችላሉ?” እና “ሙታን ያላቸው የተረጋገጠ ተስፋ” እንደሚሉ ያሉ ርዕሶችን ይዳስሳል።

ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።

የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።