በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ማላመጥና ማዋሃድ የሚጠይቅ መጽሔት”

“ማላመጥና ማዋሃድ የሚጠይቅ መጽሔት”

“ማላመጥና ማዋሃድ የሚጠይቅ መጽሔት”

ዴቪድ ናይጄሪያ ውስጥ በኦባፌሚ አቮሎቮ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪ ነው። በቅርቡ በአገሩ ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ደብዳቤ ላከ:- “በሕግ ፋኩልቲ የሕግ ፍልስፍና ትምህርት ታዋቂ ፕሮፌሰር ለሆኑ የ70 ዓመት ሰው በየጊዜው ንቁ! እወስድላቸዋለሁ። አንድ ቀን ጠዋት አዲስ የወጡትን መጽሔቶች ከሰጠኋቸው በኋላ ቢሯቸው ውስጥ ለነበረ አንድ ሰው እንዲህ አሉ:- ‘አንዳንድ መጽሐፎች የሚቀመሱ ናቸው፣ ሌሎች የሚዋጡ ናቸው፣ ጥቂት የሚሆኑ ደግሞ ማላመጥና ማዋሃድ ይጠይቃሉ። ንቁ! ማላመጥና ማዋሃድ የሚጠይቅ መጽሔት ነው።’”

በሌላ ጊዜ ደግሞ ዴቪድ ከፕሮፌሰሩ ቢሮ ከወጣ በኋላ በዚያ ለነበረ ሌላ ሰው ንቁ! ጥሩ መጽሔት እንደሆነ ሲናገሩ መስማቱን ገልጿል። “ንቁ! ጥልቀት ያለው ምርምር ተደርጎበት የሚዘጋጅ እንደሆነና አንዳንድ ጉዳዮችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ሆኖም ምንም ነገር ሳይሸሽግ የሚያቀርብ መሆኑን አድንቀው ተናግረዋል። ‘መጽሔቶቹን በከፍተኛ ትኩረት ነው የማነብበው። ጸሐፊዎቹ እንደዚህ ያሉ ግሩም ትምህርቶች እንዲያዘጋጁ ጥበብ የሚሰጣቸው አምላክ መሆን አለበት’ ብለው ሲናገሩ ሰማኋቸው።”

ንቁ! የተለያዩ ርዕሶችን የሚዳስስ ትምህርት ሰጪ መጽሔት ነው። ከሁሉም በላይ አሁን ያለውን ሥርዓት የሚተካ ሰላም የሰፈነበት አዲስ ዓለም እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ፈጣሪ በሰጠው ተስፋ ላይ እምነታችንን እንድንገነባ ያስችለናል። አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ይህን የአምላክ ዓላማ የሚያብራራ ሲሆን የእርሱን ተቀባይነት ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን ለማሳየት ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።

አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።