በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሰው ልጅ የፈጣሪን ጥበብ ይኮርጃል

የሰው ልጅ የፈጣሪን ጥበብ ይኮርጃል

የሰው ልጅ የፈጣሪን ጥበብ ይኮርጃል

የወረቀት ያህል ስስ ከሆነ መስታወት የተሠሩ የኤሌክትሪክ አምፑሎችን በአምፑል ማቀፊያ ውስጥ ለማስገባት ጫን አድርገን ስንይዛቸው የማይሰበሩት ለምንድን ነው? ሃው ኢን ዘ ዎርልድ? የተሰኘው መጽሐፍ እንደሚለው ምስጢሩ ያለው አምፑሉ “በእንቁላል ቅርጽ” የተሠራ በመሆኑ ላይ ነው። የእንቁላል ቅርፊት በጣም ስስ ቢሆንም ወፏ እንቁላሎቹን ለማቀፍ ስትቀመጥባቸው አይሰበሩም። ይህ የሆነበት ምክንያት የእንቁላሉ ቅርጽ በወፏ ክብደት ሳቢያ የሚፈጠረውን ጫና ለመቋቋም የሚያስችል ጥንካሬ ስለሚሰጠው ነው። (ቅርፊቶቹ ጠንካራ ቢሆኑ ኖሮ ጫጩቶቹ ሲፈለፈሉ ሰብረው መውጣት አይችሉም ነበር።) ሰዎችም ይህን የፈጣሪ ንድፍ በመኮረጅ የእንቁላል ቅርጽ ያላቸው አምፑሎች ሠርተዋል። በመሆኑም አምፑሉ ጠበቅ ተደርጎ ሲያዝ “ክብ ቅርጽ ያለው መሆኑ ጫናው ከተያዘበት ቦታ ወደ ሁሉም አቅጣጫ እንዲሠራጭ ያደርጋል።” ስለሆነም ልክ እንደ እንቁላሉ ጫናው በአንድ ቦታ ላይ ብቻ ስለማያርፍ አምፑሉ አይሰበርም። የሰው ልጅ ተፈጥሮን በማጥናት ብዙ ትምህርት አግኝቷል!