በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

እጽዋት—የመድኃኒት ምንጮች

እጽዋት—የመድኃኒት ምንጮች

እጽዋት—የመድኃኒት ምንጮች

በዘመናችን ሰዎች ከሚጠቀሙባቸው መድኃኒቶች መካከል አንድ አራተኛ የሚሆኑት በሙሉም ሆነ በከፊል የሚቀመሙት ከእጽዋት እንደሆነ ባለሙያዎች ይገምታሉ። ከእጽዋት የተለያዩ መድኃኒቶችን የሚያዘጋጁ ሰዎችም ብዙውን ጊዜ ይህን ሐቅ ሲጠቅሱ ይሰማል።

ለመድኃኒት ቅመማ በሚያገለግሉ እጽዋት ላይ የተደረገው አብዛኛው ምርምር ያተኮረው ፈዋሽነት ያላቸውን ንጥረ ነገሮች ነጥሎ በማውጣቱ ሥራ ላይ ነው። ለዚህ ዓይነተኛ ምሳሌ የሚሆነው አስፕሪን ሲሆን ይህ መድኃኒት የሚቀመመው ሳሊሲን የተባለ ንጥረ ነገር ካለበት ዊሎው ከተባለ ዛፍ ቅርፊት ነው።

ፈዋሽነት ያላቸው ንጥረ ነገሮች ተለይተው ከወጡ በኋላ ተመጥነው ሊሰጡ ይችላሉ። አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ እንዲህ ይላል:- “አስፕሪን የሚሰጠውን ጥቅም ለማግኘት የዊሎው ዛፍ ቅርፊት ከመውሰድ ወይም ደግሞ ዲጂታሊስ የተባለው ለልብ ሕመምተኞች የሚሰጥ መድኃኒት የሚሰጠውን ጥቅም ለማግኘት ፎክስግሎቭ የተባለውን ተክል ከመውሰድ ይልቅ በእንክብል መልክ የተዘጋጀውን መውሰድ በእጅጉ ይመረጣል።”

በሌላ በኩል ደግሞ ለመድኃኒት ቅመማ ከሚያገለግሉ እጽዋት ላይ ተፈላጊ ንጥረ ነገሮችን ለይቶ ማውጣት የራሱ የሆነ ችግር ሊኖረው ይችላል። በመጀመሪያ ደረጃ፣ በተክሉ ውስጥ ያሉት ሌሎች ንጥረ ነገሮች በምግብነትና በመድኃኒትነት ሊሰጡ የሚችሉትን ጥቅም በሙሉ ማጣት ማለት ሊሆን ይችላል። ከዚህም ሌላ በሽታ አማጭ የሆኑ አንዳንድ ተሕዋስያን እነዚህን በሽታዎች ለመፈወስ ተብሎ የሚሰጡትን መድኃኒቶች ስለለመዷቸው በቀላሉ አይሞቱም።

መድኃኒት ለመሥራት ከሚያገለግል ተክል ውስጥ ተፈላጊ ንጥረ ነገሮችን ነጥሎ ማውጣት የራሱ የሆነ ችግር እንዳለው ለማየት ሲንኮን ከተባለ ዛፍ ቅርፊት የሚቀመመውን ክዊኒን የተባለ የወባ መድኃኒት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ክዊኒን አብዛኞቹን የወባ አማጭ ጥገኛ ነፍሳት መግደል የሚችል ቢሆንም ሳይገድላቸው የቀሩት ነፍሳት ግን በዚህ አጋጣሚ በከፍተኛ መጠን ይባዛሉ። አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ “እንዲህ ዓይነቱ መድኃኒትን የመቋቋም ችሎታ በሕክምናው መስክ የሚያጋጥም አቢይ ችግር ነው” በማለት ይናገራል።

[በገጽ 24 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

አስፕሪን የሚቀመመው ዊሎው ከተባለ ከዚህ ዛፍ ነው

[ምንጭ]

USDA-NRCS PLANTS Database/Herman, D.E. et al. 1996. North Dakota tree handbook

[በገጽ 24 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

ክዊኒን የሚገኝበት የሲንኮን ዛፍ

[ምንጭ]

Courtesy of Satoru Yoshimoto