በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የኢየሱስ ሕይወት—ከፍ አድርገን የምንመለከተው ስጦታ

የኢየሱስ ሕይወት—ከፍ አድርገን የምንመለከተው ስጦታ

የኢየሱስ ሕይወት—ከፍ አድርገን የምንመለከተው ስጦታ

ከዛሬ 2,000 ዓመት ገደማ በፊት አምላክ ለሰው ልጆች ከሁሉ የላቀውን ስጦታ ሰጠ። ይህ ስጦታ የዘላለም ሕይወት የማግኘት አጋጣሚ የከፈተልን የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት ነው። (ዮሐንስ 3:16) ብዙዎች ለዚህ ስጦታ ካላቸው አመስጋኝነት የተነሳ በአራቱ ወንጌሎች ላይ ተመሥርቶ የኢየሱስን ሕይወት የሚያብራራውን እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው የተባለውን መጽሐፍ ለወዳጆቻቸውና ለዘመዶቻቸው ሰጥተዋል።

ከተወሰነ ጊዜ በፊት አንድ ሰው የገና ካርድ ለላኩለት ሰዎች ይህን መጽሐፍ እንደሰጣቸው ተናግሮ ነበር። ከኢንሳይክሎፒዲያ፣ ከመዝገበ ቃላትና ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማስረጃዎችን ጠቅሶ የገናን በዓል ማክበር ያቆመበትን ምክንያት በመግለጽ አጠር ያለ ደብዳቤ ጻፈላቸው። ከደብዳቤው ጋር እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው የተባለውን መጽሐፍ አያይዞ ላከላቸው።

ሰውየው የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች ከሆኑ ሰዎች ሁለት በጣም አበረታች የሆኑ ደብዳቤዎች እንዳገኘ ገልጿል። እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው የተባለውን መጽሐፍ በተመለከተ የደረሰው አንደኛው ደብዳቤ እንዲህ ይላል:- “የላክልን ግሩም ስጦታ . . . ደርሶናል። መጽሐፉን በጣም ወድደነዋል። መጽሐፉ አስደሳች የሆኑ ብዙ ገጽታዎች አሉት። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ከመጽሐፉ ብዙ ጥቅም አግኝተናል።”

ይህ መጽሐፍ የኢየሱስን የስብከት እንቅስቃሴ እንዲሁም የተናገራቸውን ምሳሌዎችና ያከናወናቸውን ተአምራት አካትቶ ይዟል። በተቻለ መጠን ክንውኖቹን በቅደም ተከተል ለማስቀመጥ ጥረት ተደርጓል። በተጨማሪም መጽሐፉ የኢየሱስንና በዘመኑ የነበሩትን ሰዎች ስሜት ለማሳየት የቀረቡ በሚገባ የታሰበባቸው ማራኪ ሥዕሎች ይዟል።

እርስዎም ይህን ባለ 448 ገጽ መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።