በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘ውድ በሆኑ እውነቶች የተሞላ’

‘ውድ በሆኑ እውነቶች የተሞላ’

‘ውድ በሆኑ እውነቶች የተሞላ’

በኢሊኖይ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በማይድን በሽታ ለተያዙ ሰዎች አካላዊም ሆነ ስሜታዊ እንክብካቤ የሚሰጥ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑ አንድ ሰው የምትወዱት ሰው ሲሞት የተሰኘውን ብሮሹር የገለጹት ከላይ በሠፈሩት ቃላት ነበር። ይህን ብሮሹርና አንድ የንቁ! መጽሔት ቅጂ በፖስታ ቤት በኩል የላከችላቸው መጽሔቱን ስታነብ ራሳቸውን ከሚያጠፉ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በዕድሜ የገፉ ሰዎች መሆናቸውን የተገነዘበች አንዲት የይሖዋ ምሥክር ነበረች። የተቋሙ ዳይሬክተር ጽሑፎቹ ሲደርሷቸው ምላሽ ለመስጠት ጊዜ አላጠፉም።

ዳይሬክተሩ የምትወዱት ሰው ሲሞት የተሰኘው ብሮሹር ውድ በሆኑ እውነቶች የተሞላ መሆኑን ሲገነዘቡ “ይህ ብሮሹር በያዘው ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ጥበብና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንዲሁም ማብራሪያዎች ይጽናናሉ ብዬ የማስባቸው ቤተሰቦች እንዲያገኙት ማድረግ ብችል ደስ ይለኛል” በማለት ጻፉ።

ጽሑፎቹን የላከችላቸው የይሖዋ ምሥክርም ወዲያውኑ ለዳይሬክተሩ ስልክ ደወለችላቸውና በግንባር የሚገናኙበትን ቀጠሮ ያዘች። ዳይሬክተሩ የብሮሹሩን 20 ቅጂዎች ያዘዙ ሲሆን ተቋሙ ወደፊት ተጨማሪ ቅጂዎች ስለሚያስፈልጉት በየሁለት ወይም በየሦስት ወሩ እየመጣች እንድታነጋግራቸው ጥያቄ አቀረቡ።

ምናልባት እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሌላ ሰው ይህን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር በማንበብ መጽናኛ ማግኘት ትችሉ ይሆናል። ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።

የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።