‘መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ’
‘መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ’
አንዲት ሴት በቅርቡ የታተመውን ‘መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ’ የተሰኘውን የመጽሐፍ ቅዱስ ካርታዎችን የያዘ የእንግሊዝኛ ብሮሹር ከተመለከተች በኋላ “እንደዚህ ያለ ግሩም መሣሪያ እፈልግ ነበር” ስትል ጽፋለች። “በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ የሚገኙት ቦታዎች፣ ሰዎችና ሁኔታዎች አሁን ሕያው ሆነውልኛል።”
ይህ 36 ገጾች ያሉት ባለ ቀለም ብሮሹር የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች በአምላክ ቃል ውስጥ የተገለጹ ክንውኖችን በዓይነ ኅሊናቸው መመልከት እንዲችሉ ይረዳቸዋል። ከላይ የተገለጸችው ሴት እንደሚከተለው በማለት አክላ ጽፋለች:- “ቤተ መቅደሱ በዙሪያው ካለው አካባቢ ጋር ሲወዳደር በከፍታ ቦታ ላይ እንደሚገኝ ስመለከት የይሖዋ አምልኮ ‘ከፍ ከፍ’ እንደሚል የሚናገሩትን ጥቅሶች ለመረዳት አስችሎኛል። የመማጸኛ ከተሞቹ እንዲሁም በዕብራይስጥም ሆነ በግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ የተጠቀሱት ሌሎች ቦታዎች የሚገኙበትን አካባቢ በግልጽ መመልከቱ በጣም ጠቃሚ ነው። በዚህ ማራኪ ብሮሹር አማካኝነት የሐዋርያት ሥራን መጽሐፍ ማጥናት ጀምሬያለሁ።”
ይህች ሴት ደብዳቤዋን ስትደመድም “ከአሁን በኋላ የአምላክን ቃል ሳነብብ ይህንን ግሩም ስጦታ አዘውትሬ እጠቀምበታለሁ” ብላለች።
‘መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ’ የተሰኘውን ይህንን ብሮሹር ማግኘት ከፈለጉ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ ‘መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ’ የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።