በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ብልህ እናት

ብልህ እናት

ብልህ እናት

አስተዋይና አሳቢ የሆነች እናት ልጆቿ ገንቢ ምግብ እንዲያገኙ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ታደርጋለች። መንፈሳዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላትም እንዲሁ ከዚህ ባልተናነሰ ተግታ ትጥራለች።

በቅርቡ በብራዚል የምትኖር አንዲት ሴት በዚያ አገር ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ደብዳቤ በመጻፍ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ለተሰኘው ብሮሹር ያላትን አድናቆት እንደሚከተለው በማለት ገልጻለች:- “ብሮሹሩ በጣም አስደስቶኛል። አምላክ ስለሚጠላቸው ድርጊቶች የሚገልጸውን ትምህርት ስመለከት ይህንን ጠቃሚ ሐሳብ የ10 እና 11 ዓመት ዕድሜ ላላቸው ሁለት ሴቶች ልጆቼና 5 ዓመት ለሆነው ወንድ ልጄ ልነግራቸው እንደሚገባ ተገነዘብኩ።” አክላም “ስለ አምላክ መንገዶች ለቤተሰቤ ለማስተማር የሚረዳ እንደዚህ ያለ ጽሑፍ ማግኘቴ በእርግጥም ጠቃሚ ነው!” ብላለች።

ይህቺ ሴት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ተጨማሪ ጽሑፎች እንዲላኩላትም ጠይቃለች። እርስዎም እንደዚህች ሴት ለራስዎም ሆነ ለቤተሰብዎ መንፈሳዊ ምግብ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተሰኘውን ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።

አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።