በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ከአምላክ ጋር መሄድ” በተባለው የአውራጃ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል!

“ከአምላክ ጋር መሄድ” በተባለው የአውራጃ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል!

“ከአምላክ ጋር መሄድ” በተባለው የአውራጃ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል!

▪ በዚህ ዓመት በዓለም ዙሪያ በመቶዎች በሚቆጠሩ ቦታዎች በሚካሄዱት የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚደረጉት 19 የአውራጃ ስብሰባዎች የመጀመሪያው የሚካሄደው ከመስከረም 10-12 ሲሆን የመጨረሻው ደግሞ ከጥቅምት 29-31, 2004 ይሆናል። አብዛኛውን ጊዜ ከዓርብ እስከ እሁድ ለሦስት ቀናት ከሚደረጉት ከእነዚህ የአውራጃ ስብሰባዎች መካከል እርስዎ በሚኖሩበት አካባቢም የሚካሄድ ስብሰባ ይኖራል።

በአብዛኛዎቹ ቦታዎች በሦስቱም ቀናት ስብሰባው የሚጀምረው ጠዋት 3:30 ላይ በሚሰማው ሙዚቃ ነው። የዓርብ ዕለት ጭብጥ “መንገዱ ይህ ነው፤ በእርሱ ሂድ” ይላል። “የተሰበሰብነው ይሖዋ መንገዱን እንዲያስተምረን ነው” በሚል ርዕስ የመክፈቻው ንግግር ከቀረበ በኋላ ከአምላክ ጋር በታማኝነት ከሚመላለሱ ወንድሞችና እህቶች ጋር ቃለ ምልልስ የሚደረግበት ክፍል ይከተላል። “ራሳችሁን ፈትኑ” እና “የአምላክ ቃል በየዕለቱ እርምጃችሁን እንዲመራላችሁ ፍቀዱ” የሚሉት ንግግሮች ከቀረቡ በኋላ የጠዋቱ ክፍለ ጊዜ “ሁከት በነገሠበት በዚህ ዘመን ከአምላክ ጋር መሄድ” በሚለው የስብሰባውን ጭብጥ የሚያብራራ ንግግር ይደመደማል።

ዓርብ ከሰዓት በኋላ “የሆሴዕ ትንቢት ከአምላክ ጋር እንድንሄድ ይረዳናል” በሚል ጭብጥ ሦስት ተከታታይ ንግግሮች ይቀርባሉ። ቀጥሎም “‘እግዚአብሔር ያጣመረውን’ እናንተ አትለያዩት” እና “ቅዱስ ለሆኑት ስብሰባዎቻችን አክብሮት ማሳየት” የሚሉ ንግግሮች ይኖራሉ። በዕለቱ የሚቀርበው የመጨረሻው ንግግር “ለሰዎች ሁሉ የሚሆን ምሥራች” የሚል ሲሆን ከሁሉም ቋንቋዎች ለተውጣጡ ሰዎች ምሥራቹን ለመስበክ ጥረት እንድናደርግ ያበረታታል።

የቅዳሜ ዕለት ጭብጥ “እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ” ይላል። በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ “የምሥራቹ አገልጋዮች በመሆን እድገት ማድረግ” በሚል ርዕስ ሥር ተከታታይ ንግግሮች የሚቀርቡ ሲሆን ሌላ ቋንቋ ለሚናገሩ ሰዎች እንዴት ልንመሰክር እንደምንችል የሚገልጹ ተጨማሪ ሐሳቦች ይዟል። የጠዋቱ ክፍለ ጊዜ “ከይሖዋ ጋር ለመሄድ ቃል መግባት” በሚለው ጠቃሚ ንግግር ይደመደማል፤ ከዚያም ለጥምቀት ብቃቱን ያሟሉ እጩዎች ይጠመቃሉ።

ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ “‘ዕንቅፋት’ የሚሆኑ ነገሮችን አስወግዱ” እና “መንፈስ የሚያድሱ ጤናማ መዝናኛዎች” የሚሉ ንግግሮች ይኖራሉ። ቀጥሎ የሚቀርቡት “ይሖዋ እረኛችን ነው፣” “ዘመኑን በሚገባ ዋጁ” እና “ብርሃኑ እየደመቀ በሚሄደው መንገድ ላይ መጓዝ” የሚሉ ንግግሮች አበረታች ቃለ ምልልሶች ይዘዋል። የዕለቱ ስብሰባ የሚደመደመው “የፍርዱ ሰዓት ደርሷልና ‘ነቅታችሁ ጠብቁ’” የሚል ርዕስ ባለው ትኩረት የሚስብ ንግግር ይሆናል።

‘በእውነት መመላለሳችሁን ቀጥሉ’ የሚለው የእሁዱ ስብሰባ ጭብጥ “ወጣቶች—በጽድቅ ጎዳና ተመላለሱ” በሚለው ንግግር ላይ ጎላ ተደርጎ ይብራራል። ከዚያ የሐዋርያው ጳውሎስን አገልግሎት የሚያሳይ በጥንታዊ አለባበስ የሚተወን ድራማ ይቀርባል። ቀጥሎም ከድራማው የምናገኛቸውን ትምህርቶች የሚከልስ ንግግር ይኖራል። ከሰዓት በኋላ “ከአምላክ ጋር መሄድ አሁንም ሆነ ለዘላለም በረከት ያስገኛል” በሚል ርዕስ የሕዝብ ንግግር ይቀርባል።

እርስዎ በሚኖሩበት አካባቢ ስብሰባው የሚካሄድበትን ቦታ ለማወቅ ከፈለጉ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ በመሄድ አሊያም ለዚህ መጽሔት አዘጋጆች በመጻፍ መጠየቅ ይችላሉ።