በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ማንበቤን ማቋረጥ አልቻልኩም”

“ማንበቤን ማቋረጥ አልቻልኩም”

“ማንበቤን ማቋረጥ አልቻልኩም”

ይህን አስተያየት የሰጠችው የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል! የተባለውን መጽሐፍ ያነበበች ሌኒታ የተባለች ሴት ናት። በጻፈችው የአድናቆት ደብዳቤ ላይ እንዲህ ብላለች:- “የሚገርም ነው! በመጀመሪያ አሰልቺ ታሪክ መስሎኝ ነበር፤ አንዴ ከጀመርኩት በኋላ ግን ማንበቤን ማቋረጥ አልቻልኩም። መግቢያው፣ ታሪክ ቀመስ ልብ ወለድ ይመስላል፤ ጀምሬ እስክጨርሰው ድረስ በዳንኤል ዘመን እንዳለሁ ተሰምቶኝ ነበር። ስለ ዳንኤል ትንቢት እንዲህ ያለ እውቀት አልነበረኝም።”

አክላም እንዲህ ብላለች:- “ከዚህም በላይ መጽሐፉ በዓለም ላይ ስለተነሱት ኃያላን መንግሥታት፣ ስላደረጓቸው ጦርነቶችና ስለ ሕዝቦቻቸው የሚተርክ ታላቅ የታሪክ መጽሐፍ ነው። ትንሽ ልጃችንም ይህን መጽሐፍ ማንበብ የጀመረች ሲሆን አንብባ እንድትጨርስና ለታሪክ ትምህርቷ እንድትጠቀምበት ላበረታታት አስቤያለሁ።”

እርስዎም የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል! የተባለውን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል! የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።