በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የዘመናችን ደግ ሳምራዊ

የዘመናችን ደግ ሳምራዊ

የዘመናችን ደግ ሳምራዊ

ሜክሲኮ የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው

ብዙውን ጊዜ ደጉ ሳምራዊ እየተባለ ስለሚጠራው ርኅሩኅ ሰው የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ አብዛኞቻችን ሰምተነዋል። (ሉቃስ 10:29-37) ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ምሳሌ ሲናገር አንድ ሳምራዊ በሥቃይ ላይ ለነበረ ሰው ከሚጠበቀው በላይ ፍቅራዊ እርዳታ እንዳደረገለት ገልጿል። በዛሬው ጊዜ የደጉ ሳምራዊ ዓይነት ሰዎች ይገኛሉ? ከሜክሲኮ የተላከውን የሚከተለውን ዘገባ ተመልከት።

ከሽርሽር በመመለስ ላይ የነበሩት ቤቱኤልና ቤተሰቡ ቤታቸው ለመድረስ ጥቂት ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው አውራ ጎዳናው ላይ ከባድ የመኪና ግጭት በመመልከታቸው መኪናቸውን አቁመው አደጋው የደረሰባቸውን ሰዎች ለመርዳት ሄዱ። ከተጋጩት አሽከርካሪዎች መካከል አንዱ የሕክምና ዶክተር ሲሆን ነፍሰ ጡር የሆነችውን ሚስቱንና ሁለት ትንንሽ ሴቶች ልጆቹን በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል ወስደው እንዲያሳክሙለት ጠየቃቸው። ሆስፒታል ካደረሷቸው በኋላ ቤቱኤል ተጨማሪ እርዳታ ለመስጠት አደጋው ወደደረሰበት ቦታ ተመልሶ መጣ።

ቤቱኤል እንዲህ ይላል:- “የፌደራል የአውራ ጎዳና ቃኚ ጓድ አባላት በቦታው ደርሰው የነበረ ሲሆን በአደጋው ሳቢያ የአንድ ሰው ሕይወት በማለፉ ጉዳዩ እስኪጣራ ድረስ ዶክተሩ በቁጥጥር ሥር ዋለ። ዶክተሩ እንድረዳው ያነሳሳኝ ምን እንደሆነ ሲጠይቀኝ፣ እኔም ሆንኩ ቤተሰቤ የይሖዋ ምሥክሮች እንደሆንና መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎችን እንድንወድ እንደሚያስተምር ገለጽኩለት። ከዚያም ለባለቤቱና ለልጆቹ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ስለምናደርግላቸው ስለ እነርሱ መጨነቅ እንደሌለበት ነገርኩት። በዚህ ጊዜ በአመስጋኝነት ስሜት ዓይኑ እንባ አቀረረ፤ ከዚያም በእጁ የነበሩትን ውድ ንብረቶች በሙሉ እንዳስቀምጥለት ሰጠኝ።”

ቤቱኤልና ቤተሰቡ የዶክተሩን ሚስትና ልጆች ቤታቸው አሳርፈው ለበርካታ ቀናት ተንከባከቧቸው። ቤቱኤል አጋጣሚውን ተጠቅሞ መጽሐፍ ቅዱስ ያስጠናቸው ጀመር። ዶክተሩ ከእስር ከተፈታ በኋላ የተሰማውን አመስጋኝነትና ለይሖዋ ምሥክሮች ያደረበትን ከፍተኛ አድናቆት ገለጸላቸው። በሚኖርበት ከተማ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታቸውን እንደሚቀጥሉ ቃል የገባ ከመሆኑም ሌላ ባለቤቱ ወንድ ልጅ ከወለደች ለልጁ ቤቱኤል የሚል ስም እንደሚያወጣለት ነገራቸው። ቤቱኤል እንዲህ ብሏል:- “ከሁለት ዓመት በኋላ በቅርቡ ሄደን ጠይቀናቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ እያጠኑ መሆናቸውንና የትንሹ ልጃቸው ስም ደግሞ ቤቱኤል መሆኑን ሳውቅ በጣም ተገረምኩ!”

[በገጽ 29 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ቤቱኤል