በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ብዙ ለውጥ እንዳደርግ ረድቶኛል”

“ብዙ ለውጥ እንዳደርግ ረድቶኛል”

“ብዙ ለውጥ እንዳደርግ ረድቶኛል”

ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ የተባለውን አዲስ መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) አስመልክቶ ይህን የጻፈው በቨርጂኒያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖር የ12 ዓመት ልጅ ነው። ከዚህ በፊት ፈጽሞ የማያውቃቸውንና ያልሰማቸውን ነገሮች ከመጽሐፉ ላይ መማሩን ተናግሯል። እንዲህ ሲል ገልጿል:-

“ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ የተባለው መጽሐፍ አምላክን እንድወድ፣ ላገኘሁት ሰው ሁሉ ስለ እርሱ እንድናገርና ወደ እርሱ እንድጸልይ አስተምሮኛል። አምላክ እንዲረዳኝና ከክፉ ነገር እንዲጠብቀኝ መጠየቅ እንዳለብኝም ከመጽሐፉ ላይ ተምሬያለሁ። አምላክን የሚወድድና ትእዛዛቱን የሚያከብር ማንኛውም ሰው ምድር ገነት ስትሆን በዚያ እንደሚኖር አውቄያለሁ።

“ብዙ ለውጥ እንዳደርግ ረድቶኛል። ከዚህ በፊት ሁልጊዜ እዋሽ ነበር፤ መጽሐፉን ማንበብ ከጀመርኩ በኋላ ግን መዋሸት አቁሜያለሁ። ከዚህ መጽሐፍ ላይ የተማርኳቸው ነገሮች እንደዚህ ዓይነት ተጨማሪ መጽሐፎችን የማንበብ ፍላጎት አሳድሮብኛል። በመሆኑም ስለ አምላክ የሚናገር መጽሐፍ ባገኝና ስለ እርሱ ብዙ ባውቅ ደስ ይለኛል።”

የዚህን መጽሔት ያህል ስፋት ያለውንና በውስጡ ግሩም የማስተማሪያ ሥዕሎች የያዘውን ይህን ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ ቢያነብቡ እርስዎም ተመሳሳይ ስሜት ሊያድርብዎት እንደሚችል ይሰማናል። “ኢየሱስ እንድንጸልይ አስተምሮናል፣” “ስለ ደግነት የተሰጠ ትምህርት፣” “ደስተኛ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?” እና “መዋሸት የሌለብን ለምንድን ነው?” የሚሉትን ዓይነት ምዕራፎች ማንበብዎ ያስደስትዎ ይሆናል። እርስዎም ይህን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።