በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሐዘንተኞችን ያጽናናሉ

ሐዘንተኞችን ያጽናናሉ

ሐዘንተኞችን ያጽናናሉ

በሜክሲኮ፣ ጃሊስኮ የምትገኝ አንዲት ሴት በዚያው በሜክሲኮ ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ የሚከተለውን ጥያቄ በደብዳቤ አቅርባለች:- “እባካችሁ የምትወዱት ሰው ሲሞት የሚል ርዕስ ያለውን ብሮሹር በርከት አድርጋችሁ ላኩልኝ። በእርግጥ የይሖዋ ምሥክር አይደለሁም፤ ሆኖም አብዛኞቹን ትምህርቶቻችሁን አምንባቸዋለሁ።”

ሴትየዋ ጥያቄውን ያቀረበችበትን ምክንያት እንዲህ ስትል ገልጻለች:- “ይህን ብሮሹር ላኩልኝ ያልኳችሁ አበባ ለመግዛት ወደ ሱቃችን ለሚመጡት አንዳንድ ደንበኞች ብሰጣቸው ይጠቅማቸዋል ብዬ ስላሰብኩ ነው። በመቃብር ላይ የሚቀመጥ የአበባ ጉንጉን ስለምንሸጥ አንዳንድ ጊዜ ሚስት፣ ልጅ ወይም ባል የሞተባቸው ሰዎች ይመጣሉ። ይህ ብሮሹር ትልቅ እርዳታ እንደሚያበረክትላቸው ይሰማኛል።”

በተመሳሳይ እርስዎም ሆኑ ሌላ የሚያውቁት ሰው ይህንን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር በማንበብ መጽናኛ ማግኘት ትችሉ ይሆናል። ብሮሹሩ እንደሚከተሉት ላሉ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል:- ከሐዘኔ ልጽናና የምችለው እንዴት ነው? ሌሎች እንዴት መርዳት ይችላሉ? ሙታን ምን ተስፋ አላቸው?

እርስዎም ይህን ብሮሹር ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።